የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 1-2 ፋሲል ከነማ

የ12ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞች ከሱፐር ስፖርት ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ – ፋሲል ከነማ

ስለጨዋታው

ትልቁ ነገር ተከታዮቻችን ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዲያ ሆሳዕና ነጥብ ሲጥሉ ማሸነፋችን ነው። ሆኖም 2-0 መርተን የበለጠ ማስፋት ሲገባን ያንን አጥተን ሀዋሳ ግብ አስቆጥሮብናል። መከላከሉም ማጥቃቱንም ላይ ለማመጣጠን ተቸግረናል። ዋናው ነገር ግን ነጥቡን ይዘን ለመውጣት ፍላጎቱ ስለነበር ማሸነፋችን ትልቅ በራስ መተማመን የሚሰጠን ነው። በተከታታይ ስድስት ጨዋታ አለመሸነፍ መልካም ጉዞ ነው ፤ በፋሲል ታሪክም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ይህንን ለረጅም ጊዜ ማስኬድ እንፈልጋለን።

ይሁን እንዳሻው በበዛብህ መለዮ ስለመቀየሩ

ሀዋሳዎች ያላቸው ዕድል ከ 2-0 ተጭኖ መጫወት ነው። ስለዚህ የመከላከል ባህሪውም ጥሩ ስለሆነ ይሁንን ማስገባታችን 4-1-4-1 የነበርነውን ወደ 4-2-3-1 ቀይረን ውጤቱን የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ የተጠቀምነው ነው።

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – ሀዋሳ ከተማ

ስለጨዋታው

ሲጀመር እኛ እንዳሰብነው አልነበረም። ከገባን ጀምሮ ትንሽ መዘናጋቶች ይታዩ ነበር። የመጀመሪያው 15 ደቂቃ ላይ ክፍተቶች ነበሩብን። ከዕረፍት በኋላ ግን የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገናል።

ኤፍሬም ዘካሪያስ በጉዳት መቀየሩ ስለነበረው ተፅዕኖ

ኤፍሬም ያው የጨዋታ አቀጣጣያችን ነው። የሜዳውን ምቹነት የምንጠቀመው በእንደሱ ዓይነት ተጨዋቾች ነው። አጋጣሚ ሆኖ ተጎድቷል። ያው ወንድምአገኝ ገብቶም ውጤቱ ባይሳካም ከዕረፍት መልስ ጥሩ ተንቀሳቅሰናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ