ሀዲያ ሆሳዕና ከ ጅማ አባ ጅፋር – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎችን እነሆ !

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ባለፉት ጨዋታዎች በማጥቃቱ ረገድ የነበረባቸውን ድክመት ለማስተካከል የተጨዋቾች አለመሟላት ፈተና እንደሆነባቸው ገልፀው ዛሬ ግን ሦስት አጥቂዎችን ለመጠቀም ማሰባቸውን የጠቆሙ ሲሆን ከቡናው ጨዋታ ባደረጓቸው ሁለት ለውጦች አምስት ቢጫ ካርድ ቅጣት ላይ የሚገኘው ሱለይማን ሀሚድን ለመጀመርያ ጊዜ ቋሚ በሆነው ፀጋሰው ደማሙ ሚካኤል ጆርጅን ከጉዳት ባተመለሳው ዳዋ ሆቴሳ ተክተዋል።

የመጀመሪያውን ድል ማሳካታቸው በክለቡ ዙሪያ ያሉ አካላትን ያነቃቃ መሆኑን የገለፁት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በዛሬው ጨዋታ የራሳቸው አቀራረብ ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚገቡ ገልፀዋል። ሲዳማን የረታው ስብስባቸውን ላይ ለውጥ ሳያደርጉም ለዛሬው ጨዋታ መቅረብን ምርጫቸው አድርገዋል።

ፌደራል ዳኛ ቢኒያም ወርቅአገኘሁ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የዛሬው የቡድኖቹ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
15 ፀጋሰው ደማሙ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
25 ተስፋዬ በቀለ
17 ሄኖክ አርፌጮ
23 አዲስ ህንፃ
13 አልሀሰን ካሉሻ
10 አማኑኤል ጎበና
7 ዱላ ሙላቱ
22 ቢስማርክ አፒያ
12 ዳዋ ሆቴሳ

ጅማ አባ ጅፋር

99 አቡበከር ኑሪ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
18 አብርሀም ታምራት
10 ሙሉቀን ታሪኩ
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ


© ሶከር ኢትዮጵያ