ከጊዜው ጋር ለመራመድ የሚታትረው ዳኛ…

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዳኞች በጨዋታ ላይ ከሚኖራቸው ሚና ውጭ አንድ ዳኛ በሌላ ተግባር ብቅ ብሏል።

በሀገራችን የእግርኳስ ዳኝነት ከነብዙ ችግሮቹ ዘመን ተሻግሮ እዚህ ደርሷል ፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ራሳቸውን ከወቅቱ ጋር ለማራመድ የሚጥሩ እንዲሁም በየጊዜው ራሳቸውን የሚበያበቁ ጥቂት ምስጋን ዳኞችን እንመለከታለን።

እንደሚታወቀው የእግርኳስ ዳኝነት ስህተት የሚያጣው ባይሆንም በሀገራችን እግርኳስ የሚስተዋሉ አብዛኛዎቹ ስህተቶች በዳኞች መካከል የሚስተዋል የመናበብ ችግር እና የህግ አተረጓገም ክፍተቶች መሆናቸው በስፋት ይነሳል።

የዳኝነት ሒደት ላይ. የሚስተዋሉ ስህተቶችን ለመቀነስ የዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እገዛ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ለአብነትም የጨዋታ ዳኞችን እርስ በእርስ የሚያገናኘው የተግባቦት መሳርያ በሀገራችን የተወሰኑ ዳኞች በራሳቸው ወጪ ይህን መሳርያ ገዝተው የጨዋታ ዳኝነታቸውን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል። ባሳለፍነው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ ያደረጉትን ጨዋታ በመሐል ዳኝነት የመሩት አርቢቴር ዮናስ ካሣሁን ይህን መሳርያ 40,000 ብር ያህል ወጪ በማድረግ በዚሁ ጨዋታ ላይ ጥቅም ላይ ሲያውሉት መመልከታችን በመልካም ጎኑ የሚጠቀስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ