ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ መጀመር አስቀድሞ እነዚህን መረጃዎች ይጋሩ።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በጅማ አባ ጅፋራ ከተሸነፈው ቡድናቸው ውስጥ ሁለት ለውጦችን ሲያደርጉ ፍቅሩ ወዴሳን በመሳይ አያኖ ማማዱ ሲዲቤን በአዲሱ አቱላ ለውጠዋል።

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከባህር ዳር ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ በቀይ ካርድ ቅጣት የሌለው በረከት ወልዴን ብቻ በአበባየሁ ሀጅሶ ከመለወጥ በቀር የተቀረው ስብስባቸውን የሚጠቀሙ ይሆናል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡ አርቢትር ናቸው።

የዛሬው የቡድኖቹ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ሲዳማ ቡና

30 መሳይ አያኖ
3 አማኑኤል እንዳለ
2 ፈቱዲን ጀማል
24 ጊት ጋትኮች
12 ግሩም አሰፋ
16 ብርሀኑ አሻሞ
6 ዮሴፍ ዮሐንስ
10 ዳዊት ተፈራ
15 ተመስገን በጅሮንድ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
11 አዲሱ አቱላ

ወላይታ ድቻ

99 መክብብ ደገፉ
9 ያሬድ ዳዊት
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
19 አበባየሁ አጅሶ
27 መሳይ አገኘሁ
8 እንድሪስ ሰዒድ
21 ቸርነት ጉግሳ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
13 ቢኒያም ፍቅሩ


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ