ሀድያ ሆሳዕና ወሳኝ ዝውውር ፈፀመ

በቅርቡ ወሳኝ አጥቂውን ያጣው ሀድያ ሆሳዕና በዛሬው ዕለት ወሳኝ አጥቂ አስፈርሟል።

በአሰልጣኝ አሸናፊ የሚመሩት ሆሳዕናዎች በዛሬው ዕለት የኡመድ ኡኩሪን ዝውውር አጠናቀዋል። በ2006 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እና ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ያጠናቀቀው የቀድሞ የመከላከያ አጥቂ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከለቀቀ በኋላ በ2007 ወደ ግብፅ ሊግ አምርቶ አል-ኢትሀድ አሌክሳንድሪያ፣ ኤንፒ፣ ኤል-ኤንታግ ኤል-አርቢ ስሞሀን እና አስዋን ሲጫወት መቆየቱ ይታወሳል።

በጠንካራ ምቶቹ የሚታወቀው በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው አጥቂ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቆይቶ በመጨረሻም ነብሮቹን ተቀላቅሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ