ሁለተኛው ዙር የከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀን ተራዘመ

የከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን ላይ ለውጥ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን በሦስት ምድብ ተከፍሎ በሰላሳ ሦስት ክለቦች መካከል ሲደረግ ቆይቷል፡፡ የምድብ ለ ተስተካካይ ጨዋታዎች ብቻ ዛሬ. ከሰዓት ከተደረጉ በኃላ የአንደኛው ዙር ሙሉ በሙሉ የሚጠናቀቅ ሲሆን ለቀጣዮቹ ሀያ አምስት ቀናት ክለቦች በእረፍት ላይ ይሰነብቱና የሁለተኛውን ዙር ውድድራቸውን በቀጣዩ ወር የሚጀምሩ ይሆናል፡፡ ቀደም ብሎ የከፍተኛ ሊግ አወዳዳሪው አካል ለክለቦች በላከው ደብዳቤ የሁለተኛው ዙር የሚጀመርበት ቀን መጋቢት 7 በማለት የገለፀ ቢሆንም አሁን ደግሞ በድጋሚ ስድስት ቀናት ተገፍተው ማለትም መጋቢት 13 የሁለተኛው ዙር እንዲጀመር አወዳዳሪው አካል የቀን ማስተካካያን ማድረጉን በድጋሚ ለክለቦቹ ገልጿል፡፡

የ2013 የከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የምድብ ሀ በሀዋሳ፣ የምድብ ለ በወልዲያ እና የምድብ ሐ በነቀምቴ ከተሞች እንዲደረጉ መወሰኑ ይታወሳል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ