የ14ኛውን ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንድትካፈሉ ጋብዘናል።
አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ተጋጣሚያቸው መሀል ሜዳ ላይ ከያዘው ስብስብ አንፃር የእርሳቸው ቡድን መሀል ላይ ጠቅጠቅ ብሎ መልሶ ማጥቃትን ምርጫው እንደሚያደርግ የገለፁ ሲሆን ከሀዋሳ ነጥብ ከተጋራው ቡድን ውስጥ ኢታሙና ኬይሙኒን በእንዳለ ከበደ ምትክ ተጠቅመዋል።
ሰሞንኛውን የቡድኑን መልካም አቋም በሁለተኛውም ዙር ማስቀጠል እንደሚያስቡ የተናገሩት አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ቡድናቸው በተለመደው አቀራረቡ እንደሚቀጥል አንስተዋል። ከፋሲሉ ጨዋታ ቡድኑ ያደረጋቸው ለውጦችም ጉዳት የገጠማቸው አብዱልሀቪዝ ቶፊቅ እና ታደለ መንገሻን በዳንኤል ኃይሉ እና ያሬድ ሀሰን የተካባቸው ሆነዋል።
ፌደራል ዳኛ ሚኬኤል ጣዕመ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለማምራት ተመድበዋል።
ድሬዳዋ ከተማ
30 ፍሬው ጌታሁን
2 ዘነበ ከበደ
14 ያሬድ ዘውድነህ
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
17 አስቻለው ግርማ
19 ኢታሙና ኬይሙኒ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ
ሰበታ ከተማ
1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
3 መስዑድ መሀመድ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
6 ዳንኤል ኃይሉ
24 ያሬድ ሀሰን
7 ቡልቻ ሹራ
16 ፍፁም ገብረማርያም
© ሶከር ኢትዮጵያ