ቡርትካናማዎቹ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋል

ከሰዓታት በፊት ሄኖክ ገምቴሳን ያስፈረሙት ድሬዳዋ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።

ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ዐወት ገብረሚካኤል ነው። ከኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድን የተገኘው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዐወት አሳዳጊ ክለቡን ካገለገለ በኋላ ወደ ጅማ አባጅፋር ቀጥሎም ወደ ስሑል ሽረ አምርቶ መጫወቱ ይታወሳል። ባለፈው የውድድር ዓመት ሊጉ ከመቋረጡ በፊት ወደ ወልዋሎ አምርቶ የነበረው ተጫዋቹ በክልሉ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ግማሹን ዓመት ሳይጫወት ቆይቶ አሁን ብርቱካናማዎቹን ተቀላቅሏል።

ሁለተኛው አዲስ ተጫዋች የግብ ዘቡ ወንድወሰን አሸናፊ ነው። የቀድሞ የሙገር፣ ወላይታ ድቻ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ስሑል ሽረ ግብ ጠባቂ ወደ ወልዋሎ አምርቶ የነበረ ቢሆንም የትግራይ ክልል ክለቦች በሊጉ አለመሳተፋቸውን ተከትሎ በዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ መጫወት ሳይችል ቀርቶ ነበር። አሁን ግን መዳረሻው የምስራቁ ክለብ ድሬዳዋ ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ