እዮብ ዓለማየሁ ወደ ቡድኑ ሊመለስ ነው
በቅርቡ ከቡድኑ መቀነሱን ተከትሎ ቅሬታውን አሰምቶ የነበረው እዮብ ዓለማየሁ ወደ ቡድኑ እንዲመለስ ሊደረግ ነው።
የመስመር አጥቂው ከቀናት በፊት ከቡድኑ የተቀነሰበት ምክንያት አሳማኝ አለመሆኑን፣ ውል እያለው እንደተቀነሰ እና የህክምና ክትትል ክለቡ እያደረገለት አለመሆኑን ጠቅሶ ቅሬታውን ለሶከር ኢትዮጵያ ማቅረቡ ይታወቃል። አሁን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው ከሆነ እዮብ ከቡድኑ አስቀድሞ የተቀነሰው የአቅም ችግር ኖሮበት ሳይሆን የጤናው ሁኔታ ለጨዋታ ዝግጁ የማያደርገው እንደሆነ እና ቡድኑ ከነበረበት የውጤት ስጋት አኳያ የማይጫወት ከሆነ ቡድኑን በሱ ቦታ ሰው በመተካት የተሻለ ውጤት ለማምጣት በማሰብ እንደሆነ የክለቡ አመራሮች ጠርተው በማናገር በኃላም በቡድን መሪው አማካኝነት መቀነሱ እንደተነገረው ገልፀዋል። አሁን ግን የህክምና (MRI) ምርመራ ውጤቱ እንደሚያሳየው ከሆነ መጫወት የሚያስችለው የጤና ሁኔታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከነገ ጀምሮ ወደ ባህር ዳር በመሄድ ቡድኑን እንዲቀላቀል መወሰኑን ሰምተናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የሊጉ መሪ ንግድ ባንክ እና ተከታዩ ኤሌክትሪክ ሲያሸንፉ ሀዋሳ እና መከላከያ ነጥብ ተጋርተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዳማ ሲከወኑ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ንግድ ባንክ በግብ ሲንበሸበሽ ተከታዩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ...
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ቅጣት ተላለፈባቸው
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል። ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ዕድሜ የቀረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...
አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን ሸኝቷል
ከወረጅ ቀጠናው ለመውጣት እየጣረ የሚገኘው አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን በዲሲፕሊን ምክንያት ከስብስቡ መቀነሱ ታውቋል። በ28ኛ ሳምንት ከመከላከያ ጋር ያለ ጎል...
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ተጠባቂው ጨዋታ ነጥብ በመጋራት ተጠናቋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ስድስት ጨዋታዎች ዛሬ በሁለት ስታዲየሞች ሲደረጉ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ...
ድሬዳዋ ከተማ የዛሬውን ጨዋታ መነሻ በማድረግ ቅሬታውን አቅርቧል
በ28ኛው ሳምንት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ቀትር ላይ የተጫወተው ድሬዳዋ ከተማ ለሊጉ የበላይ አካል የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል። በባህር ዳር ስታዲየም...
ሪፖርት | ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል
በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አንድ አቻ ተለያይተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ለምንም የተረቱት...