ነብሮቹ የአማካያቸውን ውል አድሰዋል

በአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ሀዲያ ሆሳናዎች የወሳኝ አማካያቸውን ውል አራዝመዋል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አራተኛ ደረጃን ይዘው በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ አለሁ የሚሉት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ከቀናት በፊት የመድሃኔ ብርሃኔን ውል ማደሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል። በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ቡድኑ በዛሬው ዕለት ደግሞ የተስፋዬ አለባቸውን ውል ማራዘሙ ታውቋል።

የቀድሞ የሰበታ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወልድያ እና ወላይታ ዲቻ ተጫዋች የነበረው ተስፋዬ በዘንድሮ የሊግ ውድድር ጥሩ ግልጋሎቱን ለክለቡ እየሰጠ ይገኛል። የተጫዋቹ ውሉን ማደስም ለአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጥሩ ዜና መሆኑ ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ