አዳማ ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ አስቀድሞ እነዚህን መረጃዎች እንድትካፈሉ ጋብዘናል።

አዲስ ተሿሚው አሱልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ዕረፍት ማድረግን መርጠው የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎች ገፍተው ሲመጡ አዳማን መያዛቸውን የገለፁ ሲሆን ኃላፊነቱ ከባድ ቢሆንም ማስተካከያዎችን በማድረግ ቡድኑን ማትረፍ እንደሚቻል በማመናቸው ወደ አዳማ እንደመጡ ተናግረዋል። በርከት ያሉ ለውጦች ይጠበቅ በነበረበት ቡድን ውስጥም ጉዳት እና ቅጣት ያገኛቸው ደስታ ጊቻሞ ፣ ትዕግስቱ አበራ ፣ ደሳለኝ ደባሽ እንዲሁም ክለቡን የለቀቀው ሙጃይድ መሀመድ ቦታ አሚኑ ነስሩ ፣ ኤልያስ አህመድ ፣ ጀሚል ያዕቆብ እና ብሩክ መንገሻ ተተክተዋል። ዳንኤል ተሾመም በታሪክ ጌትነት ምትክ ግብ ጠባቂነቱን ይዟል።

በተጨዋዎች ዝውውር ቡድኑን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው እስካሁን ግን አንድ ተጨዋች ማዘወወር ላይ ብቻ እንደታሳካላቸው ያነሱት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጨዋታው ወደ ሁለት ዲጂት ነጥብ ለማደግ ከፍ ያለ ፉክክር እንደሚደረግበት ገልፀዋል። አሰልጣኙ እንዳሉትም አዲስ ፈራሚያቸው አማኑኤል ተሾመ በሙሉቀን ታሪኩ የተተካበት ለውጥ ከሀዲያ ሆሳዕናው የተደረገ ብቸኛ ማስተካከያ ሆኗል።

ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው ናቸው

የቡድኖቹ የዛሬ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

አዳማ ከተማ

30 ዳንኤል ተሾመ
13 ታፈሰ ሰርካ
28 አሚኑ ነስሩ
6 እዮብ ማቲያስ
5 ጀሚል ያዕቆብ
26 ኤልያስ አህመድ
18 ብሩክ መንገሻ
8 በቃሉ ገነነ
9 በላይ አባይነህ
7 ፍሰሀ ቶማስ
10 አብዲሳ ጀማል

ጅማ አባ ጅፋር

99 አቡበከር ኑሪ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
6 አማኑኤል ተሾመ
18 አብርሀም ታምራት
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ


© ሶከር ኢትዮጵያ