ጅማ አባጅፋር ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል
አሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን በመሾም ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት እየጣሩ የሚገኙት ጅማ አባጅፋሮች ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸው ታውቋል።
ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ሥዩም ተስፋዬ ነው። የቀድሞው የመብራት ኃይል፣ ደደቢት እና ከ2010 ጀምሮ ደግሞ ለመቐለ 70 እንደርታ እየተጫወተ ቆይቶ በመጀመሪያው ዙር የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ወደ ሠራተኞቹ አቅንቶ ግልጋሎት የሰጠው ሥዩም ከሳምንታት በፊት ከወልቂጤዎች ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ በዛሬው ዕለት አዲስ ቡድን አግኝቷል። ለረጅም ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተጫወተው ተጫዋች ጅማን መቀላቀልም በደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ ላይ ላለው ክለብ ጥሩ ዜና ነው።
ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ የግብ ዘቡ በረከት አማረ ነው። በወልዋሎ፣ አውሥኮድ እና ኢትዮጵያ ቡና የተጫወተው በረከት በክረምቱ ወደ መቐለ አምርቶ የነበረ ቢሆንም ክለቡ በሊጉ እየሳተፈ አለመሆኑን ተከትሎ በዚህ ዓመት ሳይጫወት ቆይቶ በዘንድሮው ውድድር ሁለተኛ ብዙ ግብ ያስተናገደውን ክለብ ለማጠናከር እንዲሁም ከአቡበከር ኑሪ እና ጃኮ ፔንዜ ጋር ተፎካክሮ የክለቡ ቋሚ የግብ ዘብ ለመሆን ጅማ ደርሷል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
ተዛማጅ ፅሁፎች
የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 1-2 ወላይታ ድቻ
በ86ኛው ደቂቃ ቢኒያም ፍቅሬ ባስቆጠራት ግብ ወላይታ ድቻዎች የጅማ አባ ጅፋርን በሊጉ የመቆየት ተስፋን አጣብቂኝ ከከተቱበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ...
ሪፖርት | ወላይታ ድቻ ከድል ጋር ሲታረቅ የጅማ አባ ጅፋር መጨረሻ ቀርቧል
በሁለተኛ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻዎች ከመመራት ተነስተው ጅማ አባ ጅፋርን ሲረቱ የጅማ በሊጉ የመቆየት ነገር ወደ መጨረሻው ተጠግቷል። ጅማ...
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ተጠባቂው ጨዋታ ነጥብ በመጋራት ተጠናቋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ስድስት ጨዋታዎች ዛሬ በሁለት ስታዲየሞች ሲደረጉ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ...
ቅድመ ዳሰሳ | የ28ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች
ነገ ቀጥለው በሚደረጉት የሊጉ ሦስት ጨዋታዎች ዙሪያ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተናል። ጅማ አባ ጅፋር ከ ወላይታ ድቻ የጨዋታ ቀኑ ረፋድ ላይ...
ድሬዳዋ ከተማ የዛሬውን ጨዋታ መነሻ በማድረግ ቅሬታውን አቅርቧል
በ28ኛው ሳምንት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ቀትር ላይ የተጫወተው ድሬዳዋ ከተማ ለሊጉ የበላይ አካል የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል። በባህር ዳር ስታዲየም...
ሪፖርት | ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል
በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አንድ አቻ ተለያይተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ለምንም የተረቱት...