በአስራ አራተኛው ሳምንት የተመዘገቡ ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዕውነታዎችን እንዲህ አሰናድተናል።
– እንደባለፈው ሳምንት ሁሉ በዚህ ሳምንት 16 ጎሎች በስድስት ጨዋታዎች ተቆጥረዋል።
– በዚህ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ በሙሉ ጎል ተቆጥሯል። ይህም ከስምንተኛው ሳምንት በኋላ የመጀመርያ ነው።
– ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ ሆሳዕና በዚህ ሳምንት ጎል ሳያስቆጥሩ የወጡ ቡድኖች ናቸው።
– እንዳለፈው ሳምንት ሁሉ በዚህም ሳምንት በርካታ ጎሎች የተቆጠሩት ከእረፍት በኋላ ነው። 11 ጎሎች በሁለተኛው ሲቆጠሩ አምስት ጎሎች ከእረፍት በፊት ተመዝግበዋል።
– ከተቆጠሩት ጎሎች መካከል እዮብ ማቲያስ ያስቆጠረው በሁለተኛ ቅጣት ምት ነው። ይህም በውድድር ዓመቱ የመጀመርያ ነው።
– ከአስራ ስድስት ጎሎች መካከል ሁለት (ያሬድ ባዬ እና ዳዊት ተፈራ) በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥሩ ሄኖክ ኢሳይያስ በቀጥታ ቅጣት ምት አስቆጥሯል። ሦስት ከቅጣት ምት፣ ሁለት ከማዕዘን ምት መነሻቸውን ያደረጉ ኳሶች ወደ ጎልነት ተቀይረዋል። ሌሎቹ 7 ኳሶች የተቆጠሩት በክፍት የጨዋታ እንቅስቃሴ ነው።
– ሄኖክ ኢሳይያስ ከቅጣት ምት ያስቆጠረው በዚህ ሳምንት ከሳጥን ውጪ ተመትቶ የተቆጠረ ብቸኛ ጎል ነው።
– የወላይታ ድቻው ፀጋዬ ብርሀኑ በዚህ ሳምንት በግንባር ገጭቶ ጎል ያስቆጠረ ብቸኛ ተጫዋች ነው።
– እንዳለፈው ሳምንት በዚህም 13 ተጫዋቾች ለቡድናቸው ጎል አስቆጥረዋል። (በቃሉ ገነነ በራሱ ላይ ያስቆጠረ ተብሎ ተመዝግቧል።)
– አቡበከር ናስር እና ፍፁም ገብረምርያም በሁለት የሳምንቱ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሲሆኑ ቀሪዎቹ አንድ አንድ ጎል አስቆጥረዋል።
– ሄኖክ ኢሳይያስ፣ እዮብ ማቲያስ፣ ያሬድ ባዬ፣ ወሰኑ ዓሊ እና ሳዲቅ ሴቾ የዓመቱ የመጀመርያ ጎላቸውን በዚህ ሳምንት አስቆጥረዋል።
– 7 ተጫዋቾች ለጎል በማመቻቸት አስተዋፅኦ አድርገዋል።
የዲሲፕሊን ቁጥሮች
– በዚህ ሳምንት 33 የማስጠንቀቂያ ካርዶች ተመዘዋል። ይህም ካለፈው ሳምንት በአስር ጨምሯል።
– ሀብታሙ ገዛኸኝ በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ የወጣ የዚህ ሳምንት ብቸኛ ተጫዋች ነው።
– ወንድማገኝ ማርቆስ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ቢጫ ካርድ በመመልከት ቀጣይ ጨዋታ የሚያልፈው ተጫዋች ሆኗል።
የሳምንቱ ስታቶች
(ቁጥሮቹ የተገኙት ከሱፐር ስፖርት ነው)
ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ
ከፍተኛ – ድቻ፣ ሰበታ፣ አዳማ እና ጊዮርጊስ (6)
ዝቅተኛ – ሆሳዕና (2)
ጥፋቶች
ከፍተኛ – ድሬዳዋ (22)
ዝቅተኛ – ሰበታ እና ፋሲል (12)
ከጨዋታ ውጪ
ከፍተኛ – ድሬዳዋ (8)
ዝቅተኛ – ጅማ እና ጊዮርጊስ (2)
የማዕዘን ምት
ከፍተኛ – ባህር ዳር (11)
ዝቅተኛ – ጅማ አባ ጅፋር (2)
የኳስ ቁጥጥር ድርሻ
ከፍተኛ – ሰበታ ከተማ (62%)
ዝቅተኛ – ድሬዳዋ ከተማ (38%)
© ሶከር ኢትዮጵያ