ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አዘጋጅተናል።
ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት እያሰቡ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ እና አንድ ቀን ብቻ ልምምድ አብሯቸው የሰራውን ስዩም ተስፋዬን በጨዋታው እንደሚጠቀሙ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው የጠቆሙት አሠልጣኝ ፀጋዬ የዓመቱን ሁለተኛ ድል አዳማ ከተማ ላይ ከተቀዳጀው ቋሚ የተጫዋቾች ምርጫ አንድ ተጫዋች ብቻ ቀይረዋል። በዚህም በአምስት ቢጫ ቅጣት ላይ የሚገኘውን ወንድምአገኝ ማርቆስ በአዲሱ የቡድኑ ፈራሚ ሥዩም ተስፋዬ ተክተው ወደ ሜዳ ገብተዋል።
ተጫዋቾቻችን ለማሸነፍ ካላቸው ጉጉት መነሻነት ጫና ውስጥ ገብተው እየተጫወቱ እንደሚገኝ የገለፁት አሠልጣኝ ደጋረገ ከጫናው ለመላቀቅ የዛሬውን ጨዋታ ለማሸነፍ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። በኢትዮጵያ ቡና 2-1 ከተረታው ቡድንም አሜ መሐመድን አህመድ ሁሴን ለውጠው ወደ ሜዳ ገብተዋል።
ጨዋታውን ፌዴራል ዋና ዳኛ አክሊሉ ድጋፌ በአልቢትርነት ይመሩታል።
የሁለቱ ቡድን አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-
ጅማ አባ ጅፋር
91 አቡበከር ኑሪ
28 ስዩም ተስፋዬ
16 መላኩ ወልዴ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
28 አማኑኤል ተሾመ
18 አብርሀም ታምራት
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ
ወልቂጤ ከተማ
99 ዮሃንስ በዛብህ
12 ተስፋዬ ነጋሽ
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሴ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
14 አብዱልከሪም ወርቁ
20 ያሬድ ታደሰ
18 በሀይሉ ተሻገር
10 አህመድ ሁሴን
26 ሄኖክ አየለ
© ሶከር ኢትዮጵያ