ዋልያዎቹ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋሉ

ሁለት ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ዋልያዎቹ አንድ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ማግኘታቸውን ይፋ ሆኗል።

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ 11 ከኮተዲቯር፣ ኒጀር እና ማዳጋስካር ጋር ተደልድሎ ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ ይገኛል። ከመጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮም የምድቡ አምስተኛ እና ስድስተኛ ጨዋታውን ባህር ዳር እና አቢጃን ላይ ከማዳጋስካር እና ኮትዲቯር ጋር ያከናውናል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንም ከሁለቱ ወሳኝ ጨዋታዎች በፊት ቡድኑ የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንዲያገኝ ከታንዛኒያ እና ማጋዊ ጋር ንግግር ሲያደርግ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። አሁን ይፋ በሆነ መረጃም መጋቢት 8 ከማላዊ አቻው ጋር በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ጨዋታ እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ