​ወላይታ ድቻ ከ አዳማ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

04፡00 ላይ ከሚጀምረው ጨዋታ አስቀድሞ ተከታዮቹን መረጃዎች ትጋሩ ዘንድ ጋብዘናል።

በቡድናቸው ያለው የወጣቶች ስብስብ እንደጠቀማቸው የገለፁት አሠልጣኝ ዘላለም የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎ ለመውጣት የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። አሰልጣኙ ወላይታ ድቻ ሀዲያ  ሆሳዕናን ከረታበት ጨዋታ ውስጥ ጉዳት በገጠመው አስናቀ ሞገስ እና መሳይ አገኘሁ ምትክ አዲስ ፈራሚው ጋቶች ፓኖም እና ፀጋዬ ብርሀኑን ወደ አሰላለፍ አምጥተዋል።

በጅማ አባ ጅፋር ከተረቱበት ጨዋታ አራት ለውጦች ያደረጉት አዳማ ከተማዎች በበኩላቸው አዲስ ፈራሚዎቻቸው ኤልያስ ማሞ እና ያሬድ ብርሀኑ እንዲሁም ታሪክ ጌትነት እና ደሳለኝ ደባሽን ወደ አሰላለፍ ሲያመጡ ፍሰሀ ቶማስ ፣ ብሩክ መንገሻ ፣ እዮብ ማቲያስ እና ዳንኤል ተሾመን አሳርፈዋል። የቡድኑ የተነሳሽነት መንፈስ ጥሩ እንደሆነ የገለፁት አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ከዚህ በኋላ ያሉትን እያንዳንዱ ጨዋታ ለማሸነፍ ጠንክረው እንደሚገቡ አስረድተዋል።

ፌደራል ዳኛ ዮናስ ካሳሁን ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የዛሬው የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ወላይታ ድቻ

99 መክብብ ደገፉ

9 ያሬድ ዳዊት

12 ደጉ ደበበ

26 አንተነህ ጉግሳ

16 አናጋው ባደግ

32 ነፃነት ገብረመድህን

6 ጋቶች ፓኖም

8 እንድሪስ ሰዒድ

21 ቸርነት ጉግሳ

4 ፀጋዬ ብርሀኑ

13 ቢኒያም ፍቅሩ

አዳማ ከተማ

23 ታሪክ ጌትነት

13 ታፈሰ ሰርካ

28 አሚኑ ነስሩ

 22 ደሳለኝ ደባሽ  

5 ጀሚል ያዕቆብ

26 ኤልያስ አህመድ

25 ኤልያስ ማሞ

8 በቃሉ ገነነ

9 በላይ አባይነህ 

32 ያሬድ ብርሀኑ

10 አብዲሳ ጀማል

ያጋሩ