ኢትዮጵያዊው አማካይ ብሔራዊ ቡድኑን ለመቀላቀል ማምሻውን ወደ ሀገሩ ይገባል።
በዘንድሮው የውድድር ዓመት በግብፅ ሊግ ከምስር አል-መቃሳ ጋር የተሳካ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ ለብሔራዊ ቡድን መጠራቱን ተከትሎ ዛሬ ማምሻውን ወደ ሀገሩ የሚገባ ሲሆን ከነገ በስቲያ (ረቡዕ) በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከማላዊ ጋር የሚደረገው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ላይ ለመሳተፍ ነገ ማለዳ ወደ ባህር ዳር እንደሚያቀና ሰምተናል። ከማዳጋስካር እና ከአይቮሪኮስት ጋር እስከሚደረጉት ወሳኝ ጨዋታዎች ድረስም ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አብሮ ዝግጅት እየሰራ እንደሚቆይም ይጠበቃል።
ሽመልስ በምስር አል-መቃሳ የተሳካ ዓመት እያሳለፈ የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነትንም እየመራ ሲገኝ የካቲት ወር የክለቡ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጡን በትዊተር ገፁ ላይ ተመልክተናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ