ባህር ዳር ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የአስራ አምስተኛ ሳምንት የመጨረሻ የሆነውን ጨዋታ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናቸዋል።

ከመመራት ተነስተው ሲዳማ ቡናን 2-1 ረተው ለዚህኛው ጨዋታ የቀረቡት ባህር ዳር ከተማዎች ድል ካገኙበት ጨዋታ አንድ ተጫዋች ብቻ ለውጠው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም አፈወርቅ ኃይሉን በሳምሶን ጥላሁን ለውጠዋል። በቅድመ ጨዋታ አስተያየትም የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ደረጃችንን ብቻ ሳይሆን የስነልቦና ደረጃችንን ያሳድግልናል። ከዚህ መነሻነት ጨዋታውን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን የሚል ሀሳብ ሰጥተዋል።

በ14ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጨዋታ ሁለት ግብ አስተናግደው የተሸነፉት ሀዲያዎች ከወላይታ ዲቻው ጨዋታ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ሄኖክ አርፌጮ፣ አማኑኤል ጎበና እና ዱላ ሙላቱን በአክሊሉ አያናው ፣ ተስፋዬ አለባቸው እና መድሀኔ ብርሃኔ ለውጠዋል። አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለም ከሱፐር ስፖርት ጋር በነበራቸው ቆይታ “እኛም የዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ ስላለን ጨዋታውን ማሸነፍ አለብን። እነሱም ፉክክር ውስጠ ለመግባት ጨዋታውን ለማሸነፍ እንደሚመጡ እናስባለን።”የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ለሚ ንግሴ ጨዋታውን በመሀል ዳኝ ለመምራት የተመደቡ አርቢትር ናቸው።

ቡድኖቹ ዛሬ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ባህር ዳር ከተማ

99 ሀሪሰን ሄሱ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
8 ሳምሶን ጥላሁን
7 ግርማ ዲሳሳ
14 ፍፁም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
9 ባዬ ገዛኸኝ

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
30 አክሊሉ አያናው
5 አይዛክ ኢሴንዴ
25 ተስፋዬ በቀለ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
14 መድሀኔ ብርሃኔ
8 ብሩክ ቃልቦሬ
13 አልሀሰን ካሉሻ
21 ተስፋዬ አለባቸው
22 ቢስማርክ አፒያ
12 ዳዋ ሆቴሳ


© ሶከር ኢትዮጵያ