​የአሰልጣኞች አስተያየት | ባህር ዳር ከተማ 1-0 ሀዲያ ሆሳዕና

ከጨዋታ ሳምንቱ የመጨረሻ ግጥሚያ በኋላ ተጋጣሚ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት የሰጡት አስተያየት ይህንን ይመስላል።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ባህር ዳር ከተማ

ስለጨዋታው

በመጀመሪያው ዙር አንዱ ችግራችን አንድ ጨዋታ በጥሩ ሁኔታ ካሸነፍን በኋላ በሚቀጥለው ጨዋታ ላይ ደክመን እንገኝ ነበር። በተቻለን መጠን እሱን ለማስተካከል እየሞከርን ነው። ግን አሁንም በምንፈልገው ደረጃ እየተጫወትን ነው ብለን አናስብም። ኳሱን ለማዛዟር ሞክረናል ግን የመጨረሻው የሜዳ ክፍል ላይ ብዙ ክፍት ቦታዎችን አግኝተናል ግን የውሳኔ ስህተት ይታይ ነበር።

በደረጃ ከፍ ስለማለታቸው

ወደ ፉክክር መመለሳችን እና ደረጃ ውስጥ ወዳሉት ቡድኖች መጠጋታችን ለእኛ ኃላፊነት ነው። የበለጠ ደግሞ ጠንክረን እንድንሰራ እንዲሁም ተጨዋቾቻችን በሥነ ልቦናው ረገድ የተሻለ እንዲሆኑ ይረዳናል። ዞሮ ዞሮ ወደ ዋንጫ መጠጋት እና ደረጃ ውስጥ ማጠናቀቅ ነው ህልማችን። እዛ ለመድረስ ሜዳ ላይ የምንሰራቸውን ስህተቶች እየቀነስን መምጣት ይጠበቅብናል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና

ስለጨዋታው

በመጀመሪያው 45 ደቂቃ በእንቅስቃሴ ደረጃ ጥሩ አልነበርንም። በሁለተኛው አጋማሽ ለማስተካከል ሞክረን ነበር። መከላከል ላይ ስህተት ስለነበር ተሸንፈን ወጥተናል። 

ስለቀጣይ ጨዋታዎች

ለማስተካከል እንሞክራለን ፤ እግር ኳስ ያው በስህተት የታጀበ ሥራ ነው። አስተካክለን ለመቅረብ እንሞክራለን። 

የተስፋዬ መውጣት ስለሚኖረው ከፍተት

የአማኑኤል አለመኖር ክፉኛ ቡድናችንን ጎድቶታል ፤ በጤና ዕክል ምክንያት። በቀጣይ በእሱ ቦታ አማኑኤልን እንጠቀማለን። 

                       

ያጋሩ