ከፊቱ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚጠብቁት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል።
በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚከናወነው መጪው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጋቢት ወር ከማዳጋስካር እና ኮትዲቯር ጋር እንደሚጫወት ይጠበቃል። በባህር ዳር የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ለመከታተል በቦታው የተገኙት አሰልጣኝ ውበቱ አባተም ብሔራዊ ቡድኑ ከመጋቢት 4 ጀምሮ በሚያደርገው ዝግጅት ውስጥ የተካተቱ ተጨዋቾችን ይፋ አድርገዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ ለዝግጅት ከተጠራቸው ተጫዋቾች ውስጥ ፋሲል ገብረሚካኤል ፣ ወንድሜነህ ደረጄ ፣ ኤልያስ አታሮ ፣ አምሳሉ ጥላሁን ፣ ታፈሰ ሰለሞን ፣ መስፍን ታፈሰ እና አቤል ያለው በዚህኛው ምርጫ አልተካተቱም። በሌላ በኩል ምንተስኖት ዓሎ ፣ መናፍ ዐወል ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ሽመልስ በቀለ ያሁኑን ምርጫ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሆነዋል።
የተጠሩት ተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል :-
ግብ ጠባቂዎች
ተክለማርያም ሻንቆ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ጀማል ጣሰው (ወልቂጤ ከተማ) ፣ ፍሬው ጌታሁን (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ምንተስኖት ዓሎ (ሰበታ ከተማ)
ተከላካዮች
ሱሌይማን ሀሚድ (ሀዲያ ሆሳዕና) ፣ አሥራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ያሬድ ባየህ (ፋሲል ከነማ) ፣ ቶማስ ስምረቱ (ወልቂጤ ከተማ) ፣ ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ) ፣ መናፍ ዐወል (ባህር ዳር ከተማ)
አማካዮች
አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ መስዑድ መሐመድ (ሰበታ ከተማ) ፣ አብዱልከሪም ወርቁ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ሀብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ) ፣ ሀይደር ሸረፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከተማ) ፣ ጋዲሳ መብራቴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ) ፣ ሽመልስ በቀለ (ምስር አል ማቃሳ) ፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)
አጥቂዎች
ጌታነህ ከበደ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)