ወልቂጤ ከተማ ከወላይታ ድቻ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የአስራ ስድስተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብሮች የመክፈቻ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናል።

ከጨዋታው በፊት ተጋጣሚያቸው ወላይታ ድቻ ከጨዋታ ጨዋታ ራሱን እያሳደገ እንደመጣ እና ቡድኑም ያለውን የአሸናፊነት መንፈስ ለማስቀጠል ወደሜዳ እንደሚገባ የገለፁት አሠልጣኝ ደጋረገ ይግዛው ጅማን ከመመራት ተነስተው ካሸነፉበት ጨዋታ ሁለት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ዮሐንስ በዛብህ እና ተስፋዬ ነጋሽ በጀማል ጣሰው እና ይበልጣል ሽባባው ተክተዋል።

አዳማ ከተማን አንድ ለምንም አሸንፈው ለዚህኛው ጨዋታ የቀረቡት ወላይታ ድቻዎች በበኩላቸው ከእሁዱ ጨዋታ እንድሪስ ሰዒድ፣ ነፃነት ገብረመድህን እና ቢኒያም ፍቅሩ በስንታየሁ መንግስቱን፣ መሳይ አገኘሁ እና በረከት ወልዴ ተክተው ወደ ሜዳ ገብተዋል። የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከሱፐር ስፖርት ጋር ባደረጉት የቅድመ ጨዋታ ቆይታም ጨዋታው ጠንካራ እንደሚሆን ገምተው ለተጋጣሚ ቡድን የመጫወቻ ሜዳ ላለመስጠት እንደሚታትሩ እና ተጋጣሚያቸውን በሚገባ አጥንተው እንደመጡ ገልፀዋል።

ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ተስፋዬ ጉርሙ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
16 ይበልጣል ሽባባው
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሴ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
14 አብዱልከሪም ወርቁ
20 ያሬድ ታደሰ
18 በሀይሉ ተሻገር
10 አህመድ ሁሴን
26 ሄኖክ አየለ

ወላይታ ድቻ

99 መክብብ ደገፉ
9 ያሬድ ዳዊት
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
6 ጋቶች ፓኖም
27 መሳይ አገኘሁ
20 በረከት ወልዴ
21 ቸርነት ጉግሳ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ