የዛሬው የዋልያዎቹ ጨዋታ በቴሌቪዥን ይተላለፋል

ዛሬ 10:00 በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚደረገው የኢትዮጵያ እና ማላዊ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በቀጥታ በቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ታውቋል።

ወደ 2022 ለተሸጋገረው የካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሦስተኛ ምዕራፍ ዝግጅቱን በባህር ዳር እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከወሳኞቹ የምድቡ የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች በፊት አቋሙን ለመገምገም በዛሬው ዕለት ከማላዊ አቻው ጋር ጨዋታ ያደርጋል። ይህንን የአቋም መፈተሻ ጨዋታንም የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ አማራጮቹ ለስፖርት ቤተሰቡ እንደሚያደርስ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ