ኮትዲቯር ስብስቧን ይፋ አድርጋለች

ከኒጀር እና ኢትዮጵያ ጋር ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚጠብቃቸው ኮትዲቯሮች ምሽት ላይ በጨዋታዎቹ የሚጠቀሟቸውን ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ አድርገዋል።

ወደ 2022 ለተሸጋረገው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የአህጉሪቱ ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። በምድብ 11 ከኢትዮጵያ፣ ኒጀር እና ማዳጋስካር ጋር የተደለደሉት ኮትዲቯሮችም በቀናት ልዩነት ለሚያደርጉት የምድቡ አምስተኛ እና ስድስተኛ ጨዋታ የሚጠቀሙዋቸውን ተጫዋቾች ይፋ አድርገዋል። በዚህም ፈረንሳዊው የቡድኑ አሠልጣኝ ፓትሪክ ቢዩሜ 26 ተጫዋቾችን ሲጠሩ አራት ተጫዋቾችን ደግሞ በተጠባባቂነት መያዛቸው ተነግሯል። በዚህም ሦስት የግብ ዘብ፣ ሠባት ተከላካዮች፣ ስድስት አማካዮች እና አስር አጥቂዎችን በስብስቡ ተካተዋል።

ጥሪ ከቀረበላቸው ተጫዋቾች መካከልም ትልቅ ስም ያላቸው የማንችስተር ዩናይትዶቹ ኤሪክ ቤይሊ እና አማድ ዲያሎን ጨምሮ የቶተንሃሙ ሰርጂ ኦሪየር፣ የኤሲ ሚላኑ ፍራን ኬሲ፣ የወልቭሱ ዊሊ ቦሊ፣ የአርሰናሉ ኒኮላ ፔፔ፣ የክሪስታል ፓላሱ ዊልፍሬድ ዘሃ፣ የአያክሱ ሴባስቲያን ሀለ እና የፓርማው ጀርቪኒሆ ይገኙበታል። ከዋናው ምርጫ ውጪ በፈረንሳይ (አራት) እና ቤልጅየም (አንድ) የሚጫወቱ ተጫዋቾችን በተጠባባቂነት ይዘዋል።

ምርጫው ይህንን ይመስላል

ግብ ጠባቂዎች

ሲልቪያን ግቦሆ (ቲፒ ማዜምቤ)፣ ኤሊዜ ታፔ (ሳንፔድሮ)፣ ባድራ ዓሊ (ፍሪ ስቴት)

ተከላካዮች

ኤሪክ ቤይሊ (ማን/ዩናይትድ)፣ ዊሊ ቦሊ (ወልቭስ)፣ ኦታራ ኦስማን (ቪታ)፣ ሲሞን ዴሊ (ስላቪያ ፕራሃ)፣ ዊልፍሬድ ካኖን (አል ጋርፋ)፣ ሰርጂ ኦሪዬ (ቶተንሀም)፣ ዚ ኦታራ (ጉማሬይዥ)፣

አማካዮች

ፎሴይኒ ኩሊባሊ (ኤስፔራንስ)፣ ጂኦፍሬይ ዳይ (ሲዮን)፣ ሳንጋሬ ኢብራሂም (ፒኤስቪ)፣ ኮፊ ኩዋሜ (ቲፒ ማዜምቤ)፣ ፍራን ኬሲ (ሚላን)፣ ዦን ዳንኤል አክፓ-አክፕሮ (ላዚዮ)

አጥቂዎች

ኒኮላ ፔፔ (አርሰናል)፣ ማክስ ግራዴ (ሲቫስፖር)፣ ክሬስፖ (ሁዋን ዛል)፣ አማድ ዲያሎ (ማን ዩናይትድ)፣ ጀርቪንሆ (ፓርማ)፣ ዊልፍሬድ ዛሃ (ፓላስ)፣ ላጎ ጁንየር (ማጆርፔ)፣ ጆናታን ኮጃ (አል ጋርፋ)፣ ሰባስቲያን ሀለ (አያክስ)፣ ዮሐን ቦሊ (አል ራያን)


© ሶከር ኢትዮጵያ