የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት ጉዳይ?

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የዘንድሮ ውድድር የኮከቦች ሽልማትን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።

እስከ አስራ ስድስተኛ ሳምንት ድረስ በሦስት ከተሞች የተደረው ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በዛሬው ዕለት በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል ተገምግሟል። መልካም አፈፃፀም እንደነበረው የተገለፀው ውድድሩም በድሬዳዋ እና ሀዋሳ ቀጣይ ጨዋታዎችን ያከናውናል። በብዙ መልኮች ለየት ብሎ የሚደረገውን የዘንድሮ ውድድር በቀጥታ በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ እና የስያሜ መብት እንዲኖረው ጨረታ ያወጣው አክሲዮን ማኅበሩም ለውድድሩ አሸናፊ እና ኮከቦች ለየት ያለ ሽልማት እንደሚያዘጋጅ ሲነገር ቆይቷል። ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ በዛሬው የግምገማ መርሐ-ግብር ላይ ሀሳብ ያነሱት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የሽልማቱን ጉዳይ በተመለከተ ተከታዩን ሃሳብ ተናግረዋል።

“የኮከቦችን ሽልማት በተመለከተ ከመልቲቾይዝ ጋር እየተነጋገርን ነው። በመጀመርያ ዐምና የስርጭት እና የስያሜ ጨረታውን ስናወጣ መልቲቾይዝ የሁለቱንም መብት ለመግዛት ምክረ-ሀሳብ (ፕሮፖዛል) ሲያቀርብ ያስቀመጠው ነገር አለ። የስያሜ መብቱ ላይም በአንቀፅ 17 በዓመቱ መጨረሻ ለዋንጫ አሸናፊው እና ለኮከቦች የሚሰጠውን ሽልማት እሸፍናለሁ የሚል ነጥብ አስቀምጧል። አሁን ግን እነሱ ‘ፕሮግራሙ የሚዘጋጅበትን ሆቴል ወጪ እንጂ የኮከቦችን ሽልማት ወጪ እንሸፍናለን አላልንም’ እያሉ ነው። ይህ አግባብ አይደለም። እኛ ይህንን ውል እንደ ማፍረስ ነው የምንቆጥረው። አሁን ላይ ግን ከእነሱ ጋር ንግግሮችን እያደረግን ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ