ቅዱስ ጊዮርጊስ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሾሟል

ከቀናት በፊት ከደቡብ አፍሪካዊው አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሾሟል፡፡

አሰልጣኝ ፍራንክ ነታልን ዋና አሰልጣኝ በመሆን በክለቡ የተሾሙ ሆነዋል፡፡ ክለቡ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ አሰልጣኝ ፍራንክ በእግር ኳሱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ በተለይ በአፍሪካ በማሰልጠን በቂ ልምድ ያካበቱ ሲሆኑ በርካታ ድሎችንም አሳክተዋል። ሁለት ጊዜ የኬንያ ፕሪምየር ሊግ እና አንድ ጊዜ የኬንያ ሱፐር ካፕ እንዲሁም ምርጥ ስምንት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ የእንግሊዝ ከ17 ዓመት በታች ረዳት አሰልጣኝ በመሆን የ2011 አውሮፓ ሻምፒዮንም ሆነዋል።

የዩኤፋ ፕሮፌሽናል ላይሰንስ ያላቸው አሰልጣኝ ፍራንክ ዌስትብሮም፣ ሬንጀርስና ሚድልስቦሮውን ጨምሮ ዛማሌክ፣ ኸርትስ ኦፍ ሆክና ጎርማሂያ ክለቦችን በፊትነስ፣ በዋናና ምክትል አሰልጣኝነት አገልግለዋል። ከዚህ በተጨማሪ አሰልጣኙ በ2011 የፊፋ ኮቺንግ ኢንስትራክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በተጨማሪም የዪ.ኤፋ ኢንስትራክተር በመሆን ሰርተዋል፡፡

አሰልጣኝ ፍራንክ ከስቴዋርት ሀል በመቀጠል ሁለተኛው ክለቡን ያሰለጠኑ እንግሊዛዊ ይሆናሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ