አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሰበታ ከተማ

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎችን እንዲህ እናስነብባችኋለን።

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመጨረሻ ጊዜ ሀዋሳ ከተማን የገጠሙት የዛሬዎቹ ተፋላሚዎች በየበኩላቸው ለውጦችን አድርገው ቀርበዋል። ቅዱስ ጊዮርጊሶች አራት ለውጦችን ሲያደርጉ ሄኖክ አዱኛ ፣ አብዱልከሪም መሀመድ ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና ጋዲሳ መብራቴን በምንተስኖት አዳነ ፣ ፍሪምፖንግ ሜንሱ ፣ ሙሉአለም መስፍን እና አቤል ያለው ተክተዋል። በሰበታ በኩል የተደረገው ብቸኛው ቅያሪ ደግሞ ቃልኪዳን ዘላለም በአዲስ ፈራሚው ኦሰይ ማወሊ የተተካበት ሆኗል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የቡድኖቹ የዛሬው አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ

22 ባህሩ ነጋሽ
6 ደስታ ደሙ
23 ምንተስኖት አዳነ
15 አስቻለው ታመነ
24 ፍሪምፖንግ ሜንሱ
20 ሙሉዓለም መስፍን
5 ሀይደር ሸረፋ
10 አቤል ያለው
21 ከነአን ማርክነህ
28 አማኑኤል ገ/ሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
3 መስዑድ መሀመድ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
77 ኦሰይ ማወሊ
7 ቡልቻ ሹራ
16 ፍፁም ገብረማርያም


© ሶከር ኢትዮጵያ