ከሦስት ክለቦች ጋር ዋንጫ ያሳካችው ሰናይት ቦጋለ…

በኢትዮጵያ የሴቶች እግርኳስ በክህሎታቸው ከሚጠቀሱት መካከል ናት። ዘንድሮ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተቀላቅላ እየተጫወተች የምትገኘውና ለቡድኑ ስኬት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች አንዷ የሆነችው አማካይዋ ሰናይት ቦጋለ ከዛሬው የንግድ ባንክ ድል በኋላ ባደረገችው አጭር ቆይታ የውድድር ዓመቱ አድካሚ እንደነበር ገልፃ በድል መወጣታቸው እንዳስደሰታት ተናግራለች። “ዓመቱ በጣም አልፊ እና የሚከብድ ነበር። ሁሉም ቡድኖች ጥሩ ተፎካካሪ ነበሩ። ከሌላ ጊዜ የተለዩ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።  ይህንን ተወጥተን ቻምፒዮን በመሆናችን በጣም ደስተኛ ነኝ።”
ከ2008 ጀምሮ ከቡድን ጓደኛዋ ሎዛ አበራ ጋር በደደቢት፣ አዳማ እና ባንክ (የ2012 መሰረዙ ከግምት ገብቶ) በተከታታይ ለአምስት የውድድር ዘመናት ዋንጫ ማንሳት የቻለች ሲሆን ይህም የፈጠረባትን ስሜት እንዲህ አጋርታናለች።

“በዚህ ዓመት በጣም ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ። ምክንያቱም ዓመቱን እንዳያችሁት ፈታኝ ነበር፡፡ ሁሉም ቡድኖች ተፎካካሪ እንደመሆናቸው ዋንጫ ለማንሳት ይከብድ ነበር። ይህን ተወጥተን ከሦስተኛ ክለቤ ጋር ማሳካቴ እንዲሁም የመጀመሪያ ዓመት የንግድ ባንክ ቆይታዬን በዋንጫ በማጀቤ ከምለው በላይ ደስታ ተሰምቶኛል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ