የሉሲዎቹ አምበሎች ታውቀዋል

በዛሬው ዕለት ከደቡብ ሱዳን ጋር ላለባቸው የወዳጅነት ጨዋታ ተጫዋቾቻቸውን የሰበሰቡት አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው ሦስት አምበሎችን መርጠዋል፡፡

የንግድ ባንኳ አጥቂ እና የ2013 የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢዋ ሎዛ አበራ በዋና አምበልነት ሉሲዎቹን የምትመራ ሲሆን ሌላኛዋ የሊጉ ምርጥ ግብ ጠባቂ ተብላ የተመረጠችው የመከላከያዋ ታሪኳ በርገና የሁለተኛ አምበልነት ተመርጣለች። የኢትዮ ኤሌክትሪኳ የመስመር ተከላካይ እፀገነት ብዙነህ ደግሞ ሦስተኛ አምበል በመሆን ተመርጣለች፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከነገ ጀምሮ በካፍ የልኅቀት ማዕከል ዝግጅት የሚጀምር ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ