የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ የሚደረግባቸው ሰዓታት ለውጥ ተደረገባቸው

ነገ ከሦስት ሳምንት እረፍት በኋላ ድሬዳዋ ላይ የሚጀመረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ የሚደረግባቸው ሰዓታት ላይ ለውጥ መደረጉ ተረጋግጧል።

በድሬዳዋ ያለውን ሙቀት ተከትሎ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ረፋድ ሦስት ሰዓት እና አመሻሽ አስራ አንድ ሰዓት እንዲደረጉ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ክለቦች በአንደኛ ዙር ግምገማ ወቅት የሰዓቱ ሁኔታ በድጋሚ እንዲታይ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው። በዚህም መሠረት የሊግ ካምፓኒው የድሬዳዋ ጨዋታዎች ላይ ለውጥ በማድረግ 10:00 እና ምሽት 1:00 ላይ እንዲደረጉ መወሰኑን ለክለቦች መግለፁ ታውቋል።

“የ17ኛ ሳምንት የውድድር ፕሮግራማችን ረቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2013 እንደሚጀምር ይታወቃል።
በመሆኑም ቀደም ሲል በተላከው ፕሮግራም የውድድሩ ሰዓት ጠዋት 3 ሰአት እና ከሰዓት 11 ሰዓት በሚል የተገለፀው ከዲኤስቲቪ ጋር በመነጋር ሁለቱም ውድድሮች ከሰአት 10፡00 እና ምሽት 1፡00 ላይ የተቀየሩ መሆኑን እያሳወቅን ውድድራችን የሚጀመረው ረቡዕ መጋቢት 29 2013 ከሰዓት10፡00 ላይ መሆኑን እየገለፅን በሰዓት የተስተካከለውን ፕሮግራም ነገ የምንልክ መሆኑን እንገልፃለን።” በማለት ለክለቦቹ ገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ