ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ መቀላቀሉን አስታውቋል አስፈርመዋል፡፡

የኤርትራ ዜግነት ያለው ሮቤል ተክለሚካኤል ቡናማዎቹን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው፡፡ ከክለቡ ጋር ለወር ያህል ልምምድ ሲሰራ የነበረው ይህ የመስመር እና የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች በኤርትራ ብሔራዊ ቡድን እና በኤርትራው ቀይ ባህር ክለብ ሲጫወት የሚታወቅ ሲሆን በ2019 ሴካፋ ውድድር ብሔራዊ ቡድኑ እስከ ፍፃሜ ላደረገው ጉዞ ትልቁን ሚና በመጫወት የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ መመረጡ ይታወሳል። አሁንም ደግሞ እስከ ቀጣዩ ዓመት መጨረሻ በሚቆይ ውል የኢትዮጵያውን ክለብ ተቀላቅሏል፡፡

ሁለተኛው የክለቡ ፈራሚ ናትናኤል በርኸ ነው፡፡በአማካይ እና በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ በከፍተኛ ሊጉ ካፋ ቡና እና በደደቢት የተጫወተው ናትናኤል እንደ ሮቤል ሁሉ እስከ ቀጣዩ ዓመት መጨረሻ ቡናማዎቹን መቀላቀሉ ተገልጿል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ