ቅዱስ ጊዮርጊሶች ነገ አዲስ አበባ ይመለሳሉ

ከሰበታ ጋር ነጥብ የተጋሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ነገ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ።

ቀስ በቀስ ከዋንጫው ፉክክር እየራቁ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በአዲሱ አሰልጣኛቸው ፍራንክ ነታል እየተመሩ የድሬዳዋ ጨዋታቸውን ያለ ጎል በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወቃል። ቡድኑ ነገ ጠዋት በ3:00 በረራ ወደ አዲስ አበባ የመመለሳቸው ነገር እርግጥ የሆነ ሲሆን እንደ ምክንያት በክለቡ በኩል ግልፅ የተቀመጠ መረጃ ባይኖርም በቀጣይ ሳምንት አራፊ በመሆናቸው እንዲሁም ከልምምድ ሜዳ እና ተያያዥ ጉዳዮች አለመመቸት ጋር ተያይዞ እንደሆነ ሰምተናል። በዚህም ቢሾፍቱ ወደሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው መታሰቢያ አካዳሚ በመጓዝ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ እንደሚቆዩና በ19ኛው ሳምንት በወሳኙ የሸገር ደርቢ ጨዋታ መዳረሻ ላይ ዳግመኛ ወደ ድሬዳዋ እንደሚመለሱ ለማወቅ ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ