የአሠልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 ሰበታ ከተማ

ያለ ግብ ከተጠናቀቀው የ10 ሰዓቱ ጨዋታ በኋላ አሠልጣኞች የድህረ-ጨዋታ አስተያየታቸውን ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል።

ፍራንክ ነታል – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ቡድኑ ስላልተጠቀመባቸው የግብ ማግባት አጋጣሚዎች?

እንደተባለው በርከት ያሉ የግብ ማገባት ሙከራዎችን ፈጥረን ነበር። ከምንም በላይ ግን ኳሱን ተቆጣጥሮ መጫወት እና ጥሩ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚዎችን መፍጠሩ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው።

ስለ ግብ ጠባቂው ባህሩ ነጋሽ ብቃት?

ሙሉ የጨዋታ ክፍለ ጊዜውን ተጠምዶ አልነበረም። ግን እንደጠበኩትም ጥሩ ሆኖ ነበር የተጫወተው።

ስለ ቡድኑ የመስመር ተከላካዮች እንቅስቃሴ?

ጥሩ ተጫውተዋል። ግን ሜንሱ መጠነኛ ድክመት የነበረበት ቢሆንም ቦታውን በማስጠበቅ ጥሩ ነበር። በቀጣይ ግን አደረጃጀታችን ላይ በደንብ እንሰራለን።

አብርሃም መብራቱ – ሰበታ ከተማ

ቡድኑ በርከት ያሉ የግብ ማግባት አጋጣሚዎችን ፈጥሮ ውጤታማ ስላልሆነበት ምክንያት?

ከረጅም ጊዜ በኋላ ያደረግነው የመጀመሪያ ጨዋታችን እንደመሆኑ መጠን እና የመክፈቻውን ጨዋታ በአሸናፊነት ለመወጣት ከነበረን ጉጉት መነሻነት ብዙ ኳሶችን አምክነናል። ይህ ደግሞ ዛሬ የመጀመሪያ አደለም። ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ችግሮች ነበሩብን። የተጋጣሚ የመከላከል ስፍራ ውስጥ ስንገባ ትንሽ የመረጋጋት ሁኔታዎች ይቀሩናል። ይህንን ደግሞ ማስተካከል ይጠበቅብናል። በተረፈ ግን ለሁለታችንም ጥሩ ጨዋታ ነበር።

ለቡድኑ ተጫዋቾች በተለይ ለዳዊት ሲያስተላልፈው ስለነበረው የጨዋታ ላይ መልዕክት?

ዳዊት ልምድ ያለው ተጫዋች ነው። የእኛ ተከላካዮች ኳስን ተጫውተው እንዲወጣ የሚያደርገው ደግሞ እሱ ነው። ስለዚህ በተቻለ መጠን ኳስን ተቆጣጥረን እየተጫወትን የተጋጣሚ የመከላከል ወረዳ ላይ ቶሎ እንግባ ነበር ስለው የነበረው። ይህንን ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ አስተካክለነዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ