አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ

ምሽት ላይ ከሚጀምረው ጨዋታ በፊት ተከታዮቹን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።

ባህር ዳር ላይ ድሬዳዋ ከተማን ካሸነፉበት ስብስብ ውስጥ የአንድ ተጫዋች ለውጥ ያደረጉት አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀንን በታፈሰ ሰለሞን ተክተዋል።

በሀዋሳ ከተማ በኩል ከሰበታ ከተማው ሽንፈት ሦስት የአሰላለፍ ለውጦች ተደርገዋል። በለውጦቹ አሰልጣኝ መሉጌታ ምህረት ብርሀኑ በቀለ ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና ተባረክ ሄፋሞን በአለልኝ አዘነ ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና መስፍን ታፈሰ ቦታ ተጠቅመዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ነመሀል ዳኝነት ይመራዋል።

የቡድኖቹ የዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
14 እያሱ ታምሩ
15 ሬድዋን ናስር
13 ዊሊያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሃንስ
18 ዳዊት ታደሰ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
14 ብርሀኑ በቀለ
11 ተባረክ ሄፋሞ
17 ብሩክ በየነ


© ሶከር ኢትዮጵያ