አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ

የምሽቱ ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ ቀጣዮቹን መረጃዎች አቅርበንላችኋል።

በኮቪድ ከተያዙባቸው 12 ተጫዋቾች ሰባቱ የመጀመሪያ ተሰላፊ መሆናቸው እና ውጤቱ በመጨረሻ ሰዓት የሚታወቅ መሆኑ ጨዋታውን እንደሚያከብድባቸው የገለፁት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በርካታ አስገዳጅ ለውጦች አድርገዋል። አሰልጣኙ ከወልቂጤ ከተማ ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ መክብብ ደገፉ ፣ ደጉ ደበበ ፣ አንተነህ ጉግሳ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ በረከት ወልዴ እና ፀጋዬ ብርሀኑን በዳንኤል አጄዬ ፣ ዮናስ ግርማይ ፣ መልካሙ ቦጋለ ፣ አበባየሁ አጪሶ ፣ ዲዲዬ ለብሪ እና ቢኒያም ፍቅሩ ቀይረዋል። ዳንኤል አጄዬ እና ዲዲዬ ለብሪም ለክለቡ የመጀመሪያ ጨዋታ

ጫና ባይኖርብንም አጨራረሳችንን ለማሳመር ከሀዋሳ በፊት ድሬዳዋ ላይ በትኩረት እንጫወታለን ያሉት አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ጅማ አባ ጅፋርን ከረቱበት ስብስብ ላይ ባደረጉት ብቸኛ ለውጥ ሀብታሙ ተከስተን በይሁን እንዳሻው ምትክ ተጠቅመዋል።

ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ ይህንን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።

ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ወላይታ ድቻ

30 ዳንኤል አጃዬ
9 ያሬድ ዳዊት
7 ዮናስ ግርማይ
15 መልካሙ ቦጋለ
16 አናጋው ባደግ
19 አበባየሁ ሀጪሶ
27 መሳይ አገኘሁ
11 ዲዲዬ ለብሪ
21 ቸርነት ጉግሳ
13 ቢኒያም ፍቅሩ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
17 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም


© ሶከር ኢትዮጵያ