አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ጅማ አባ ጅፋር ከ ድሬዳዋ ከተማ

የሳምንቱ ሁለተኛ ቀን መክፈቻ የሆነውን ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎችን እንሆ !

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ከፋሲል ከነማው ሽንፈት የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በለውጦቹም መላኩ ወልዴ ፣ አብርሀም ታምራት እና ሳድቅ ሴቾ በአዲስ ፈራሙዎቹ አሌክስ አሙዙ ፣ ዋለልኝ ገብሬ እና ራሂም ኦስማኖ ተተክተዋል።

በኢትዮጵያ ቡና ሲረቱ ከተጠቀሙበት ስብስብ ሁለት ለውጦችን ያደረጉት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ያለምንም ምክንያት በሙሉ ኃይላቸው ለማሸነፍ እንደሚገቡ ተናግረዋል። ቡድኑ ዛሬ በያሬድ ዘውድነህ እና ሄኖክ ገምቴሳ ምትክ በረከት ሳሙኤል እና አዲስ ፈራሚው ዳንኤል ኃይሉን በመጠቀም ጨዋታውን ይጀምራል።

አማኑኤል ኃይለስላሴ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

የተጋጣሚዎቹ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ጅማ አባ ጅፋር

91 አቡበከር ኑሪ
28 ስዩም ተስፋዬ
30 አሌክስ አሙዙ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
28 አማኑኤል ተሾመ
24 ዋለልኝ ገብሬ
8 ሱራፌል ዐወል
19 ተመስገን ደረሰ
3 ራሂም ኦስማኖ

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
6 ዐወት ገብረሚካኤል
15 በረከት ሳሙኤል
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
12 ዳንኤል ኃይሉ
17 አስቻለው ግርማ
13 ኢታሙና ኬይሙኒ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ


© ሶከር ኢትዮጵያ