አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ሲዳማ ቡና ከ አዳማ ከተማ

በምሽቱ ጨዋታ ቡድኖቹ ስለሚጠቀሟቸው ስብስቦች ቀጣዮቹ መረጃዎች ወጥተዋል።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በጥሩ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን የኮቪድ ጉዳይ ግን እክል እንደነበረባቸው ገልፀዋል። ከሀዲያ ሆሳዕናው ሽንፈት አንፃር ባደረጓቸው ላውጦችም ፍቅሩ ወዴሴ ፣ አበባየሁ ዮሐንስ ፣ ፈቱዲን ጀማል ፣ ሽመልስ ተገኝ ግርማ በቀለ እና ዮናስ ገረመውን በአዲስ ፈራሚው ፋቢያን ፋርኖሌ ፣ አማኑኤል እንዳለ ፣ ሰንደይ ሙቱኩ ፣ ጊትጋት ኮች ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ እና ማማዱ ሲዲቤ ለውጠዋል።

ከመጀመሪያ ተሰላፊዎች ስድስት ተጫዋቾችን በኮቪድ ምክንያት እንደማያገኙ የገለፁት አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በባህር ዳር ከተረቱበት ጨዋታ ስድስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ዳንኤል ተሾመ ፣ ደሳለኝ ደባሽ ፣ ጀሚል ያዕቅብ ፣ እዮብ ማቲያስ ፣ ኤልያስ አህመድ እና በላይ አባይነህ በአሰላለፉ ያልተካተቱ ሲሆን አዲስ ፈራሚዎቹ ላሚን ኩማር ፣ ሚሊዮን ሰለሞን ፣ አሊሴ ኦቢሳ ጆናታን ሀብታሙ ወልዴ እንዲሁም ታሪክ ጌትነት እና ደስታ ጌቻሞ የእነሱን ቦታ ይሸፍናሉ።

ኢብራሂም አጋዥ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።

ሲዳማ ቡና

23 ፋቢያን ፋርኖሌ
3 አማኑኤል እንዳለ
32 ሰንደይ ሙቱኩ
24 ጊትጋት ኮች
5 መሐሪ መና
16 ብርሀኑ አሻሞ
10 ዳዊት ተፈራ
34 ያሬድ ከበደ
8 ኢኪኪ አፎላቢ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
27 ማማዱ ሲዲቤ

አዳማ ከተማ

23 ታሪክ ጌትነት
13 ታፈሰ ሰርካ
20 ደስታ ጌቻሞ
28 አሚኑ ነስሩ
34 ላሚን ኩማር
80 ሚሊዮን ሰለሞን
36 አሊሴ ዴማንኬል
25 ኤልያስ ማሞ
29 ሀብታሙ ወልዴ
32 ያሬድ ብርሀኑ
10 አብዲሳ ጀማል


© ሶከር ኢትዮጵያ