አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ባህር ዳር ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

10፡00 ላይ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንድትጋሩ ጋብዘናል።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ አዳማ ከተማን ከረቱበት ጨዋታ በስብስባቸው ላይ ሦስት ለውጦችን ሲያደርጉ ሀሪሰን ሄሱ ፣ ፍፁም ዓለሙ እና ወሰኑ ዓሊ በፂዮን መርዕድ ፣ አፈወርቅ ኃይሉ እና ግርማ ዲሳሳ ተተክተዋል። አሰልጣኙ የዕረፍቱ ጊዜ ከጨዋታ መደራረብ አንፃር ተጫዋቾችን ለማሳረፍ ያለውን ጠቀሜታ ጠቁመው በኃላፊነት በተሳተፉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የፈጠረባቸውን ደስታ ገልፀዋል።

በእርሳቸው ቡድን ውስጥ የኮቪድ ወረርሺኝ የፈጠሩው ጫና ሥራቸውን የሚያካብድ እንደሆነ ነገር ግን ሁኔታው የሁሉም ክለቦች ችግር መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ከመጨረሻው ጨዋታቸው ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አዲስ ፈራሚያቸው እስራኤል እሸቱ እንዲሁም ፍሬው ሰለሞን እና ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስን በሄኖክ አየለ ፣ ያሬድ ታደሰ እና በኃይሉ ተሻገር ቦታ በመተካት ጨዋታውን ይሚጀምሩ ይሆናል።

ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ተፈሪ አለባቸው ናቸው።

ቡድኖቹ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ባህር ዳር ከተማ

22 ፂዮን መርዕድ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
8 ሳምሶን ጥላሁን
24 አፈወርቅ ኃይሉ
18 ሳለአምላክ ተገኘ
7 ግርማ ዲሳሳ
9 ባዬ ገዛኸኝ

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
16 ይበልጣል ሽባባው
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሴ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
25 ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ
14 አብዱልከሪም ወርቁ
13 ፍሬው ሰለሞን
9 እስራኤል እሸቱ
10 አህመድ ሁሴን


© ሶከር ኢትዮጵያ