10፡00 ሲል በሚጀምረው ጨዋታ ዙሪያ እነኚህን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።
በድሬዳዋ የመጀመሪያ ጨዋታቸው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ የተጋሩት ሰበታ ከተማዎች አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የጊዮርጊሱ ጨዋታ ከውድድር ዕረፍት በኋላ የነበሩባቸውን ድክመቶች እንዳሳያቸው እና ለዛሬው ጨዋታ እንዳዘጋጃቸው ጠቅሰው በቀጣይ ጨዋታዎች በተለይም የሚቆጠሩባቸውን ግቦች ለመቀነስ እንደሚጥሩ ተናግረዋል። ሰባታዎች ለዛሬው ጨዋታ ፉዓድ ፈረጃ እና ያሬድ ሀሰንን ወደ አሰላለፍ በማምጣት መስዑድ መሀመድ እና ኃይለሚካኤል አደፍርስን አሳርፈዋል።
አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በሀዋሳ ከተማ ከደረሰባቸው ሽንፈት አራት ለውጦችን አድርገዋል። በለውጦቹ ሀብታሙ ታደሰ ከረጅም ሳምንታት በኋላ ወደ አሰላለፍ ሲመለስ የአብቃል ፈረጃም ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዳሚው አሰላለፍ ውስጥ ተካቷል። ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ አማኑኤል ዮሀንስ እና ምንተስኖት ከበደም ጨዋታውን ይጀምራሉ። ወንድሜነህ ደረጄ ፣ እያሱ ታምሩ ፣ ሬድዋን ናስር እና አቤል ከበደ ደግሞ ከዛሬው አሰላለፍ ውጪ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው። አሰልጣኙ ሽንፈት ከሥነ ልቦና አንፃር የሚፈጥረውን ጫና አንስተው በፍጥነት ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ለዛሬው ጨዋታ ከፍ ያለ ትኩረት እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።
ኢንተርናሽናል አርቢትር በአማላክ ተሰማ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።
የቡድኖቹ የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል;-
ሰበታ ከተማ
1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
24 ያሬድ ሀሰን
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
8 ፉዓድ ፈረጃ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
77 ኦሰይ ማወሊ
7 ቡልቻ ሹራ
16 ፍፁም ገብረማርያም
ኢትዮጵያ ቡና
99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
22 ምንተስኖት ከበደ
2 አበበ ጥላሁን
27 ያብቃል ፈረጃ
8 አማኑኤል ዮሃንስ
13 ዊሊያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
25 ሀብታሙ ታደሰ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን
© ሶከር ኢትዮጵያ