አሰላለፍ እና ወቅታዊ ጉዳዮች – ሀዋሳ ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር

ስለምሽቱ ጨዋታ አሰላለፍ እና የተሰጡ አስተያየቶች ተከታዮቹን መረጃዎች አቅርበንላችኋል።

ኢትዮጵያ ቡናን በመርታት ከድል ጋር የታረቁት ሀዋሳ ከተማዎች ከዛ ጨዋታ አንፃር ሁለት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ላውረንስ ላርቴ እና ኤፍሬም ዘካሪያስ በፀጋአብ ዮሃንስ እና አለልኝ አዘነ ተተክተዋል። የቡድኑ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የቡናውን ድል ብዙ ሰው ላይጠብቅ ቢችልም የነበራቸው ዕድል ማሸነፍ ብቻ ስለነበር ለማሸነፍ እንደገቡ ዛሬም የተሟላ ቡድን ባይኖራቸው በድል ለማጠናቀቅ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ከቀኑ መጣበብ አንፃር የተለየ ዝግጅት ባያደርጉም የአዳራደር ለውጥ አድርገው እንደሚገቡ እና እስከመጨረሻው ድረስ የራሳቸውን ጨዋታ እየተጫወቱ እንደሚታገሉ የተናገሩት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በድሬዳዋ ከተማ ከተሸነፉበት ጨዋታ አንድ ለውጥ ብቻ ሲያደርጉ አዲስ ፈራሚያቸው ዋለልኝ ገብሬን በሳዲቅ ሴቾ ተክተዋል።

ጨዋታውን በዋና ዳኝነት የመምራት ኃላፊነቱ ለፌደራል ዳኛ እያሱ ፈንቴ ተሰጥቷል።

የቡድኖቹ የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል;-

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
44 ፀጋአብ ዮሃንስ
12 ደስታ ዮሃንስ
18 ዳዊት ታደሰ
23 አለልኝ አዘነ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
14 ብርሀኑ በቀለ
11 ተባረክ ሄፋሞ
17 ብሩክ በየነ

ጅማ አባ ጅፋር

91 አቡበከር ኑሪ
28 ሥዩም ተስፋዬ
30 አሌክስ አሙዙ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
6 አማኑኤል ተሾመ
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ
3 ራሂም ኦስማኖ


© ሶከር ኢትዮጵያ