የከሰዓቱ ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሊያውቋቸው የሚገቡ መረጃዎች…
ጨዋታው ከመጀመሩ አስቀድሞ በድሬዳዋ ከትናንቱ ጫን ያለ እና ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ጥሏል። ዝናቡ ጨዋታው ከመጀመሩ አንድ ሰዓት በፊት ያቆመ ሲሆን የወትሮው ሙቀትም ቀዝቀዝ ባለ ነፋሻማ አየር ተተክቷል። በመቀመጫ ከተማቸው ያደረጉትን የመጀመሪያ ጨዋታ በድል የተወጡት ብርቱካናማዎቹ በዛሬው ጨዋታ በጉዳት እና በአምስት ቢጫ ካርድ ቅጣት ያጧቸው አስቻለው ግርማ እና ፍሬዘር ካሳን በዘነበ ከበደ እና በሱራፌል ጌታቸው ተክተዋል።
አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ከጨዋታው በፊት ከሱፐር ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ ከጨዋታ መንገዳቸው በላይ ዋነኛ አጀንዳቸው ሦስት ነጥቡን ማሳካት ላይ እንደሆነ ገልፀው ቡድናቸው ኳስን መስርቶ በቶሎ ተጋጣሚ ሜዳ ለመድሩስ እንደሙጥር ጠቁመዋል።
ዛሬም ሙሉ ስብስባቸውን ማግኘት ያልቻሉት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የተለየ ዝግጅት ባያደርጉም ከሽንፈት ለማገገም ለማሸነፍ እንደሚገቡ እና ለማጥቃት ፍላጎት ያለው ፈጣን መልሶ ማጥቃት የሚተገብር ቡድን ይዘው እንደሚገቡ የጠቆሙ ሲሆን በፋሲል ከነማው ጨዋታ ያልተጠቀሙባቸውን ተጫዋቾች በማስገባት አራት ለውጦች አድርገዋል። በለውጦቹም አንተነህ ጉግሳ ፣ በረከት ወልዴ ፣ ነፃነት ገብረመድህን እና ጋቶች ፓኖም መልካሙቦጋለ ፣ አበባየሁ አጪሶ ፣ መሳይ አገኘው እና ዲዲዬ ለብሩን በመተካት ወደ ሜዳ ይገባሉ። ነገር ግን ቡድኑ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ግብ ጠባቂ ሳያካትት ጨዋታውን ይጀምራል።
ይህንን ጨዋታ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ፌደራል ዳኛ አዳነ ወርቁ ናቸው።
የቡድኖቹ የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል ;-
ድሬዳዋ ከተማ
30 ፍሬው ጌታሁን
6 ዐወት ገብረሚካኤል
15 በረከት ሳሙኤል
2 ዘነበ ከበደ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
12 ዳንኤል ኃይሉ
8 ሱራፌል ጌታቸው
13 ኢታሙና ኬይሙኒ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ
ወላይታ ድቻ
30 ዳንኤል አጃዬ
9 ያሬድ ዳዊት
7 ዮናስ ግርማይ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
20 በረከት ወልዴ
32 ነፃነት ገብረመድህን
6 ጋቶች ፓኖም
21 ቸርነት ጉግሳ
13 ቢኒያም ፍቅሩ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ
© ሶከር ኢትዮጵያ