አሰላለፍ እና ወቅታዊ ጉዳዮች – ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

በዛሬው የምሽት ጨዋታ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች እና የተሰጡ አስተያየቶች ይህንን ይመስላሉ።

ወልቂጤ ከተማ በባህር ዳር ከተሸነፈበት የ17ኛው ሳምንት ጨዋታ አምስት ለውጦችን በማድረግ ወደ ሜዳ ይገባል። ተከላካይ መስመር ላይ መሀመድ ሻፊ የዳግም ንጉሴን ቦታ ሲይዝ መሀል ላይ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና አብዱልከሪም ወርቁ በበኃይሉ ተሻገር እና ጂብሪል ናስር ከፊት ደግሞ እስራኤል እሸቱ እና አህመድ ሁሴን በአቡበከር ሳኒ እና ሄኖክ አየለ ተለውጠዋል። 

አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ስለዛሬው ጨዋታ ያላቸውን ኃሳብ ለሱፐር ስፖርት ሲሰጡ የሜዳው ጭቃማነት ለእንቅስቃስያቸው ፈተና እንዳይሆን ያላቸውን ስጋት ጠቁመው ከአብዱልከሪም ወርቁ እና አሳሪ አልመሀዲ ጉዳት በቀር የተሻለ ስብስብ ይዘው እንደሚቀርቡ ተናፍረዋል።

ከአዲሱ ክለባቸው ጋር የመጀመሪያውን ድል በአዳማ ከተማ ላይ ያሳኩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከአዳማው ጨዋታ አንፃር ባደረጉት ለውጥ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የወጣው ሰንደይ ሙቱኩን በፈቱዲን ጀማል ተክተዋል።

አሰልጣኝ ገብረመድህን በአስተያየታቸው አዳማው ድል የቡድናቸውን መነሳሳት ከፍ እንዳደረገው እና የዛሬ ጨዋታ ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።
ፌደራል ዳኛ ብርሀኑ መኩሪያ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።

የቡድኖቹ የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል ;-

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
12 ተስፋዬ ነጋሽ
30 ቶማስ ስምረቱ
4 መሀመድ ሻፊ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
11 ጂብሪል ናስር
18 በኃይሉ ተሻገር
13 ፍሬው ሰለሞን
8 አቡበከር ሳኒ
26 ሄኖክ አየለ

ሲዳማ ቡና

23 ፋቢያን ፋርኖሌ
3 አማኑኤል እንዳለ
2 ፈቱዲን ጀማል
24 ጊትጋት ኮች
5 መሐሪ መና
16 ብርሀኑ አሻሞ
10 ዳዊት ተፈራ
34 ያሬድ ከበደ
8 ኢኪኪ አፎላቢ
27 ማማዱ ሲዲቤ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ


© ሶከር ኢትዮጵያ