ከአፍታ ቆይታ በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ ጉዳዮችን ተከታተሉ።
ከጨዋታው ቀደም ብሎ በሱፐር የቅድመ ጨዋታ አስተያየት ላይ አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ያልተገኙ ሲሆን ምክንያቱ የኮቪድ 19 ተጠቂ በመሆናቸው እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል። እሳቸውን ተክቶ አስተያየት የሰጠው የቡድን መሪው ሀብታሙ ዘዋለ አሰልጣኙ ከመጨረሻ ልምምድ በኋላ በገጠማቸው ህመም ሳቢያ ዛሬ ቡድኑን እንደማይመሩ ገልጿል። ቡድኑ በወላይታ ድቻው ጨዋታ መጀመሪያ አሰላለፍ ከተጠቀመበት ስብስብ ውስጥ ምንም ለውጥ ሳያደርግ የዛሬውን ጨዋታ ያደርጋል።
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ቡድናቸው ወልቂጤ ከታማን ከረታበት ጨዋታ ጉዳት የገጠመው መሀል ተከላካዩ መናፍ ዐወልን በሳሙኤል ተስፋዬ የተኩበትን ብቸኛ ለውጥ አድርገዋል። አሰልጣኙ ካለፈው ጨዋታ ውጤታቸው በመነሳት እና ተጋጣሚያቸው ጥንካሬ አንፃር ተዘጋጅተው ስለመምጣታቸውም ተናግረዋል።
ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ፌደራል ዳኛ ማኑሄ ወልደፃዲቅ ናቸው።
የቡድኖቹ የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል ;-
ፋሲል ከነማ
1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
17 ሀብታሙ ተከስተ
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም
ባህር ዳር ከተማ
22 ፅዮን መርዕድ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
13 አህመድ ረሺድ
16 ሳሙኤል ተስፋዬ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
8 ሳምሶን ጥላሁን
24 አፈወርቅ ኃይሉ
18 ሳለአምላክ ተገኘ
7 ግርማ ዲሳሳ
9 ባዬ ገዛኸኝ
© ሶከር ኢትዮጵያ