ከምሽቱ ጨዋታ መጀመር አስቀድሞ ቀጣዮቹን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።
ጥሩ ከነበሩትበት ካለፈው ጨዋታ መሻሻሎችን በማድረግ ዛሬ ነጥብ ይዘው ለመውጣት እንዳሰቡ የተናገሩት አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ከሲዳማው ሽንፈት አራት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አዲስ ፈራሚ ግብ ጠባቂያቸው ሳኩራ ካማራን በታሪክ ጌትነት ቦታ ሲተኩ ጅሚል ያዕቆብ ፣ ማማዱ ኩሊባሊ እና በቃሉ ገነነን በታፈሰ ሰረካ ፣ አሚን ነስሩ እና ያሬድ ብርሀኑ ቦታ ተጠቅመዋል።
አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጥሩ የዝግጅት ጊዜ እንደነበራቸው ገልፀው እንደማንኛውም አሰልጣኝ አራቱንም የድሬዳዋ ጨዋታዎች የማሸነፍ ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል። ቡድናቸው ሀዲያ ሆሳዕናም ባህር ዳር ላይ የመጨረሻ ጨዋታውን ከሲዳማ ቡና ጋር አድርጎ ሲያሸንፍ የተጠቀመውን አሰላለፍ ሳይቀይር ለዛሬው ጨዋታ ደርሷል።
ፌደራል አርቢትር ተፈሪ አለባቸው ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
የቡድኖቹ የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል ;-
አዳማ ከተማ
1 ሳኩራ ካማራ
5 ጀሚል ያዕቆብ
20 ደስታ ጌቻሞ
36 አሊሴ ኦቢሳ ጆናታን
80 ሚሊዮን ሰለሞን
34 ላሚን ኩማር
8 በቃሉ ገነነ
25 ኤልያስ ማሞ
31 ማማዱ ኩሊባሊ
29 ሀብታሙ ወልዴ
10 አብዲሳ ጀማል
ሀዲያ ሆሳዕና
77 መሐመድ ሙንታሪ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
3 ቴዎድሮስ በቀለ
5 አይዛክ ኢሲንዴ
17 ሄኖክ አርፊጮ
21 ተስፋዬ አለባቸው
10 አማኡኤል ጉበና
13 አልሀሰን ካሉሻ
22 ቢስማርክ አፒያ
12 ዳዋ ሆቴሳ
18 ዑመድ ኡኩሪ
© ሶከር ኢትዮጵያ