የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከነማ 0-0 ባህር ዳር ከተማ

ያለጎል ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል።

ሀብታሙ ዘዋለ (ቡድን መሪ) – ፋሲል ከነማ

ስለ ጨዋታው

“አስበን ይዘን የገባነውን ነገር በመጀመሪያው አጋማሽ መተግበር አልቻልንም በሁለተኛው አጋማሽ ከልጆቻችን ጋር ተነጋግረን አሻሽለን ገብተናል።በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ተንቀሳቅሰን የግብ እድሎችንም መፍጠር ችለናል ፤ እነዛን ብንጠቀም ኖሮ ነጥብ ይዘን እንወጣ ነበር።”

እድሎችን የመጠቀም ችግሮች ስለመኖራቸው

“ምክንያት ባይሆንም ትላንትና በመዝነቡ ሜዳ እንዳያችሁት ነው ከዚህ የተነሳ ተጫዋቾቻችን የምንፈልገውን ነገር መተግበር አልቻሉም። በሁለተኛው አጋማሽ ግን በተሻለ ወደ ጎል ሙከራ ማድረግ ችለናል ፤ በዚህም አሸንፈን መውጣት ይገባን ነበር።”

ከአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ጋር ስለነበራቸው የስልክ ቆይታ

“አሰልጣኝ ስዮም ቤት ሆኖ ጨዋታውን በቴሌቪዥን እየተከታተለ ነበር ፤ እያንዳንዱን የጨዋታ ሂደት እየተከታተለ ይደውልልኝ መሻሻል የሚገባቸውን ነገሮች በደንብ እየተገናኘን እያወራን ነበር እኔም ብዙ የሱን ሀሳቦች እየፈፀምኩ ነበር።”

ውጤቱ ፍትሃዊ ነበር?

“በሁለተኛው አጋማሽ እንደነበረን ብልጫ ማሸነፍ ይገባን ነበር ፤ ነገርግን በቀጣይ አሻሽለን ለመቅረብ እንሞክራለን።”

ፋሲል ተካልኝ – ባህርዳር ከተማ

ምንም የግብ ሙከራ አለማድረጋቸው ከጉጉት ጋር የሚያያዝ ከሆነ

“በሚገባ ፤ በተለይ ወደ ተጋጣሚ የማጥቂያ ወረዳ ውስጥ ስነገባ በቁጥር እናንስ ነበር።ይህም ተከላካዮቹ ዘና ብለው እንዲጫወቱ ፈቅደንላቸው ነበር ፤ በሁለተኛው አጋማሽ የተወሰኑ ለውጦችን አድርገን ለማሻሻል ሞክረናል።እንደአጠቃላይ ግን የማናጠቃበት ሆነ ኳሶችን የምንቀባበልበት መንገድ በስህተቶች የተሞላ ነበር።”

ስለፍፁም አለሙ ቅያሬ

“ፍፁም ተቀይሮ ከገባ በኃላ በተለይ ሁኔታ ቡድኑ መሉ ለሙሉ ወደ ተቃራኒ ሜዳ መግባት ችሏል ፤ በቁጥር ብልጫ ያገኘናቸው ኳሶችም ነበሩ ግን መጠቀም ሳንችል ቀርተናል። ፍፁም ያው ከጉዳት እንደመምጣቱ እና በቂ የማገገሚያ ጊዜ ባለማግኘቱ መሉ ዘጠና ደቂቃ ልንጠቀመው አልፈቀድንም።”

በመጨረሻ ደቂቃ ስለነበረችው የፍፁም ቅጣት ምት አጋጣሚ

“ለእንቅስቃሴው እሩቅ ነበርኩ በዚህም ለመናገር ይቸግረኛል ፤ አካላዊ እንቅስቃሴ እስካለ ድረስ ግልፅ ፍፁም ቅጣት ነው።”

ውጤቱ ፍትሃዊ ነው ?

“ሁለቱም ቡድኖች ሜዳ ላይ ከነበረን እንቅስቃሴ አንፃር ፍትሃዊ ውጤት ነው።”


© ሶከር ኢትዮጵያ