አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ወላይታ ድቻ ከ ሀዋሳ ከተማ

የኮቪድ ተፅዕኖ በከባዱ ያረፈበትን ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መተጃዎችን እነሆ !

በጨዋታው ሁለቱ ተጋጣሚዎች ቀሪዎቹ ተጫዋቾቻቸው በኮቪድ 19 ቫይረስ መጠቃታቸውን ተከትሎ ወላይታ ድቻ 11 ሀዋሳ ከተማ ደግሞ 13 ተጫዋቾችን ብቻ ይዘው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ይህንን ጉዳይ አስመልክተው አስተያየታቸውን የሰጡት የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው አሰላለፍ እያወጣላቸው ያለው ኮቪድ መሆኑን ጠቁመው ባለፈው ጨዋታ አንድ ብቻ ግብ ጠባቂ የነበራቸው ሲሆን አሁን ደግሞ ሦስቱም በመኖራቸው ሁለቱን በሜዳ ላይ ተጫዋችነት እንደሚጠቀሙ ገልፀዋል። አሰልጣኙ ጨዋታው ሊከብድ እንደሚችል ግን ሰግሞ የተቻላቸውን እንደሚያደርጉም ጨምረው ተናግረዋል።

ከተጋጣሚያቸው አንፃር ሁለት ተጫዋቾችን በተጠባባቂነት የመያዝ ዕድል የኖራቸው አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትም ኮቪድ ያሳደረባቸውን ተፅዕኖ ገልፀው ድቻ ጠንካራ እና በወጣቶች የተገነባ ቡድን ስለመሆኑም ተናግረዋል።

የወላይታ ድቻዎቹ ግብ ጠባቂዎች መክብብ ደገፉ እና አብነት ይስሀቅ በሜዳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ምንተስኖት ጊንቦ እና ዘላለም ኢሳይያስን በተጠባባቂነት ይዞ ጨዋታውን ይጀምራል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ይመሩታል። የመሐል ዳኛ የሆነው ዮናስ ካሣሁንም በዚህ ጨዋታ ረዳት ሆኗል 

የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ወላይታ ድቻ

30 ዳንኤል አጃዬ
12 ደጉ ደበበ
15 መልካሙ ቦጋለ
20 በረከት ወልዴ
19 አበባየሁ አጪሶ
32 ነፃነት ገብረመድህን
27 መሳይ አገኘሁ
8 እንድሪስ ሰዒድ
21 ቸርነትጉግሳ
99 መክብብ ደገፉ
23 አብነት ይስሀቅ

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሃንስ
25 ሄኖክ ድልቢ
23 አለልኝ አዘነ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
19 ዮሃንስ ሴጌቦ
17 ብሩክ በየነ
11 ቸርነት አወሽ


© ሶከር ኢትዮጵያ