አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ጅማ አባ ጅፋር ከ ሰበታ ከተማ

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ ዙሪያ እነዚህን መረጃዎች እንድትካፈሉ ጋብዘናል።

ጅማ አባ ጅፋሮች ከሀዋሳ ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ ከተጠቀሙበት አሰላለፍ አንድ ለውጥ ያደረጉ ሲሆን በተከላካይ ቦታ ላይ በውብሸት ዓለማየሁ ቦታ ከድር ኸይረዲን ተክተዋል።

የቡድኑ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጥሩ አቋም ላይ ላለው ተጋጣሚያቸው ያላቸውን ክብር ገልፀው ሰሞኑን በስህተቶች ምክንያት የጣሏቸው ነጥቦች እንደሚያስቆጯቸው ሳይሸሸጉ አዳዲስ ተጫዋቾቻውን ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ እንደሰሩ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በኢትዮጵያ ቡና ከገጠማቸው ሽንፈት አንፃር አራት ለውጦችን አድርገዋል። በለውጦቹም ተከላካይ መስመር ላይ መሳይ ጳውሎስ እና ጌቱ ኃይለማርያም በቢያድግልኝ ኤልያስ እና ዓለማየሁ ሙለታ ሲተኩ አማካይ ክፍል ላይ አዲሱ ዩጋንዳዊ ፈራሚ ክሪዚስቶም ንታንቢ በፉዓድ ፈረጃ ምትክ የመጀመሪያ ጨዋታውን ይጀምራል። በሌላኛው ለውጥ ደግሞ ቃልኪዳን ዘላለም በፍፁም ገብረማርያም ምትክ ወደ አሰላለፍ መጥቷል።
አሰልጣኙ ከሽንፈት እና አቻ በኋላ የሚደረግ ጨዋታ በመሆኑ ለማሸነፍ እንደሚገቡ የጠቆሙ ሲሆን በኮቪድ ምክንያት የሚያጧቸው ተጫዋቾች ቢኖሩም ዝግጅታቸው ከግለሰብ ይልቅ ቡድን ላይ ስለሚያተኩር በምትካቸው የሚገቡት ተጫዋቾች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደሚወጡ ዕምነታቸውን ገልፀዋል።
ፌደራል ዳኛ አዳነ ወርቁ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የመምራቱን ኃላፊነት ወስደዋል። የመሐል ዳኛ የሆኑት ማኑሄ ወልደፃዲቅ ደግሞ በኮሮና ምክንያት ዳኞች በመመናመናቸው የረዳት ዳኛ ሆነው ይዳኛሉ።

የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ምርጫ ይህንን ይመስላል:-

ጅማ አባ ጅፋር

91 አቡበከር ኑሪ
28 ሥዩም ተስፋዬ
30 አሌክስ አሙዙ
4 ከድር ኸይረዲን
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
6 አማኑኤል ተሾመ
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ
3 ራሂም ኦስማኖ

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
14 ዓለማየሁ ሙለታ
4 አንተነህ ተስፋዬ
12 ቢያድግልኝ ኤልያስ
24 ያሬድ ሀሰን
27 ክሪዚስቶን ንታንቢ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
7 ቡልቻ ሹራ
20 ቃልኪዳን ዘላለም
77 ኦሰይ ማወሊ


© ሶከር ኢትዮጵያ