አሳላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ሀዲያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ

የዕለቱን ቀዳሚ ጨዋታ የአሰላለፍ ለውጦች እና አስተያየቶች ይህንን ይመስላሉ።

ሀዲያ ሆሳዕናዎች ከአዳማ ከተማ ካደረጉት ጨዋታ አንፃር ፀጋሰው ድማሙ፣ አዲስ ህንፃ እና መድሀኔ ብርሀኔን በአይዛክ ኢሲንዴ፣ ተስፋዬ አለባቸው እና ካሉሻ አልሀሰን ቦታ ተክተዋል። አጀማመራቸው እንዳሰቡት እንዳልነበረ ዛሬ ለማስተካከል እንደሚጥሩ የገለፁት አሰልጣኝ አሸናፊ ኮቪድ ብዙም ባያገኛቸው የሌሎቹም ችግር እንደሚያስስባቸው አንስተው ዛሬ በማጥቃት ላይ ያመዘነ አቀራረብ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ደግአረግ ይግዛው በኮቪድ ምክንያት አስተያየት ለመስጠት አልተገኙም። ጉዳዩ እንደ አሰልጣኙ ቡድን አባል ተፅዕኖ ቢኖረውም በስልክ ግንኙነት እያደረጉ ቡድኑን እንደሚመሩ የተናገሩት በቦታቸው የተተኩት ምክትል አሰልጣኙ አብዱልሀኒ ተሰማ ከስብስብ አንፃር ቡድኑ ዛሬ የኮቪድ ተፅዕኖ ቀለል እንዳለለት ተናግረዋል። ከሲዳማው ጨዋታ ጋር ሲተያይ በተደረጉ ቅያሪዎች የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው ዮናታን ፍሰሀ፣ ዳግም ንጉሣ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ እና አሜ መሀመድ ቅጣት ላይ የሚገኘው ቶማስ ስምረቱ ፣ ተስፋዬ ነጋሽ ፣ ጂብሪል ናስር እና በኃይሉ ተሻገርን ተክተዋል።

ጨዋታውን ዮናስ ካሣሁን በመሐል ዳኝነት ሲመራው እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም የረዳት ዳኞች እጥረት በመኖሩ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው በረዳት ዳኝነት ተሰይሟል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
3 ቴዎድሮስ በቀለ
15 ፀጋሰው ድማሙ
17 ሄኖክ አርፊጮ
23 አዲስ ህንፃ
10 አማኡኤል ጉበና
14 መድሀኔ ብርሀኔ
22 ቢስማርክ አፒያ
12 ዳዋ ሆቴሳ
18 ዑመድ ኡኩሪ

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
23 ዮናታን ፍስሐ
4 መሐመድ ሻፊ
19 ዳግም ንጉሤ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
13 ፍሬው ሰለሞን
14 አብዱልከሪም ወርቁ
7 አሜ መሐመድ
8 አቡበከር ሳኒ
26 ሄኖክ አየለ


© ሶከር ኢትዮጵያ