የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ዕጣ ማውጣት በዚህ ሳምንት ይደረጋል

በሁለት ከተሞች የሚደረገው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የዕጣ ማውጣት እና የውድድር ደንብ ውይይት የሚደረግበት ቀን ታውቋል፡፡

የሊጉ የ2013 የውድድር ዘመን በአርባ አምስት ክለቦች መካከል በተለያዩ ከተሞች በምድብ ተከፍሎ ሲደረግ ከቆየ በኃላ አስራ ስድስት ክለቦችን ወደ ማጠቃለያው አሳልፎ የምድብ ሙሉ ጨዋታዎች መጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ለማደግ ስድስት ቡድኖችን የሚለየው የማጠቃለያ ውድድር ሚያዝያ 27 በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአዳማ እና አሰላ ከተሞች የሚጀምር ሲሆን ለዚህም ውድድር የቅድመ ዕጣ ማውጣት ቅዳሜ ሚያዝያ 16 በአዲስ አበባ ኢሊሌ ሆቴል ይከናወናል። ከዕጣ ማውጣቱ ባለፈ ፌድሬሽኑ ከውድድሩ ደንብ ጋር በተያያዘ ከክለቦች ጋር ውይይት የሚያደርግ ሲሆን ማሻሻያ በሚደረግባቸው ላይም በስፋት ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ