የወልቂጤው አሰልጣኝ ድሬዳዋ አይገኙም

የወልቂጤ ከተማው ዋና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ድሬዳዋ አይገኙም።

አሰልጣኝ ደግአረገ በአስራ ዘጠነኛው ሳምንት ወልቂጤ በሀዲያ ሆሳዕና በተረታበት ጨዋታ ላይ በኮቪድ ምክንያት ቡድናቸውን ሳይመሩ ቀርተው ቡድኑ በምክትል አሰልጣኙ አብዱልሀኒ ተሰማ አማካኝነት ወደ ሜዳ መግባቱ ይታወሳል። አሁን ከወደ ድሬ እንደሰማነው ከሆነ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ቡድናቸውን በማሰልጠን ሥራ ላይ እንደማይገኙና ይልቁንም አዲስ አበባ መሆናቸውን አረጋግጠናል። የዚህ ምክንያት ደግሞ በድሬዳዋ ወቅት ጠብቆ የሚከሰተው ደንጊ የተባለ ህመም አጋጥሟቸው ለተሻለ ህክምና ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸውን ለማወቅ ችለናል።

ዛሬ የድሬዳዋ ቆይታቸው የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከአዳማ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ወልቂጤዎች እንደባለፈው ጨዋታ ሁሉ በምክትል አሰልጣኙ አብዱልሀኒ ተሰማ እየተመሩ እንደሚገቡ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ