ተስፈኛው ግብ ጠባቂ ህይወቱ አለፈ

በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ አዳማ ከተማ እየተደረገ ባለው ውድድር ላይ ሀዋሳ ከተማን እያገለገለ የሚገኘው ግብ ጠባቂ ትናንት አመሻሽ ህይወቱ አልፏል፡፡

በ2011 ክለቡን በመቀላቀል በዚህ ዓመት በ20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ የሚገኘው አቤል አያናው ግብ ጠባቂ ትናንት ሀዋሳ ከተማ በ12ኛው ሳምንት የምድቡ መርሀግብር ቅዱስ ጊዮርጊስን 3ለ2 ሲረታ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ይሁንና ምሽቱን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጥቃት ተሰንዝሮበት ሕይወቱ ማለፉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡

ሶከር ኢትዮጵያም በአቤል አያናው ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦች ለጓደኞቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን ትመኛለች፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ